ሰሞኑን በምንሰማው ነገር ብዙዎቻችን
ክርስቲያኖች በተለያየ ሃሳብ ውስጥ እንዳለን ይታወቃል። በተለይ የወሬ ገበያው የደራላቸው ሚዲያዎች የቤተክርስቲያንን ጉዳይ የራሳቸው
በማስመሰል ብዙዎችን ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ እየመሩ እንደሆነ በግልጽ እየታየ ነው። የቤተክርስቲያን ጉዳይ እለት እለት የሚያስጨንቃቸው
አካላት እንዳሉት ሁሉ አንድነቷና ሰላሟ ወደነበረበት ቢመለስ የእለት እንጀራቸው የሚያሳስባቸው ጥቂቶች አይደሉም። ምክንያቱም በአባቶች
መካከል የተፈጠረው ልዩነት ለወንበዴዎች ሰርግና ምላሽ ሆኖላቸው ነበር። “ ግር ግር ለሌባ ይመቻል አይደል ” የሚባለው ፣ አሁን
ስለ ሰላም ከሚጨነቁት አካላት በላይ የነበረው አለመግባባት እንዲቀጥል የሚደክሙት ወገኞች ስራ በዝቶባቸዋል። በጣም የሚደንቀው በሰላም
እና በአንድነት እየኖሩ ሁሉን ማግኘት እየተቻለ ለምን ቤተክርስቲያኒቱን በጥብጠው እራሳቸውን እንደሚበጠብጡ ነው የማይገባኝ፥ የሰላም
ሰው የፍቅር ሰው መባል በሰውም ሆነ በእግዚአብሔርም ዘንድ ያስከብራል እንጅ ውርደት የለበትም።
Saturday, December 29, 2012
Wednesday, September 19, 2012
እንደ ሙሴ ያለ መሪ ክፍል 2
በክፍል አንድ ለማየት እንደሞከርነው የሊቀነቢያት ሙሴ ህይዎት ለብዙዎቻችን
የሚያስተምረው በጎ ነገር እንዳለ ለመረዳት እንደቻልን እገምታለሁ። ዛሬም በክፍል ሁለት ከሱ ህይዎት ተነስተን በእኛ ህይዎት ሊኖር
ስለሚገባው ነገር ለማየት እንሞክራለን ስለሁሉም የአምላክ ቸርነት
የወላዲተ አምላክ አማላጅነት ከሁላችን ጋራ ይሁን።
1/ የሙሴ ትህትናቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን ከሰው ወገን እንደ ሊቀነቢያት ሙሴ ያለ ትሁት ሰው አልነበረም << ሙሴም በምድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ትሑት ሰው ነበረ። ዘኁል 12፥3
Saturday, September 15, 2012
Wednesday, August 8, 2012
እንደ ሙሴ ያለ መሪ
ወደ ሃሳቤ ከመግባቴ በፊት ጥቂት ስለ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ህይዎት ላነሳ እዎዳለሁ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ታላቅ ስምና ዝና ካላቸው ሰዎች ከፊት ልናስቀምጠው እንችላለን። ሊቀነቢያት ሙሴ ከመወለዱ አንስቶ እስከ ህልፈተ ህይዎቱ ድረስ እግዚአብሔር ታላላቅ ስራዎችን ከእርሱ ጋር ሆኖ ይሰራ ነበር።
እስራኤል ዘስጋ በግብጽ ባርነት ሳሉ ይደርስባቸው ከነበረው ሰቆቃ አንዱ ወንድ ልጅ ወልዶ ማሳደግ
የተከለከለ ነበር። ማንኛውም ልጅ ወንድ ሆኖ ከተወለደ ይገደል ነበር። ታዲያ በዚህ ዘመን ነበር ሊቀነቢያት ሙሴ የተወለደው። አስቀድሞ
በእግዚአብሔር የተወሰነ ስለነበር በባህር ቢጣልም እንኳን አንዳች
ሳይነካው በህይዎት ከባህር ሊወጣ ችሏል። ከዚህም በላይ በእግዚአብሔር ጥበብ በቤተ መንግስት በእንክብካቤ የንጉሱ ልጅ እየተባለ ነው ያደገው። ነገር ግን እሱ በቤተመንግስት ተደስቶ
ቢኖርም በወገኖቹ ላይ የሚደርሰው ግፍና መከራ እለት እለት ያንገበግበው ስለነበር። የንጉስ ልጅ መባልን አይፈልግም ነበር። በኋላም ወገኖቹ በስቃይ
ላይ እያሉ እኔ በቤተመንግስት የላመ የጣፈጠ አልበላም አልጠጣም ብሎ ወሰነ። የህዝቡን ግፍና መከራ ለማየት በሄደ ጊዜ አንድ ግብጻዊ እስራኤላዊውን ሲደበድበው
አገኘው ። በልቡ ውስጥ ቁጭት ስለነበረው ግብጻዊውን ገድሎ እስራኤላዊውን
ታድጎታል። ነገር ግን ይህን በማድረጉ ከጠላት ያዳነው ሰው መልሶ አሳልፎ ሊሰጠው እንደሚችል በመረዳቱ ከቤተመንግስት ኮብልሎ ወደ ምድያም ምድር ተሰደደ ።
Friday, June 29, 2012
ኮሶ አረህ
ይህ ቦታና አካባቢ ለአዲስ አበባ ቅርብ ቢሆንም ከመልክአምድራዊ አቀማመጡ
ገደላማነት የተነሳ ምንም አይነት የዓለም ስልጣኔ ሊደርስበት አልቻለም። ነገር ግን አስቀድሞ የተዘረጋው ሃይማኖታዊና ባህላዊ ስርዓቱ እጅግ
ሰልጥነናል ከሚሉት አካባቢዎች የተሻለ ነው። ለምሳሌ በአካባቢው አንድ ጸጉረ ልውጥ ሰው ቢታይ ሁሉም ህብረተሰብ በአይነ ቁራኛ ስለሚከታተለው
ምንነቱ በቅጽበት ይታወቃል። በዚህ የተነሳ እስከ አሁን ድረስ በአካባቢው ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ውጭ አንድም የእምነት ተቋም
አይገኝም። አንድ የሌላ እምነት ሰው በተለያየ ምክንያት ወደ አካባቢው ቢመጣ ከተወሰኑ ቀናት ውጭ እንዲኖር አይፈቀድለትም። መቆየት
ከፈለገ ስርዓተእምነቱን ተምሮ እምነቱን ተቀብሎ የመኖር ግዴታ አለበት። ካልፈለገ አይገደድም በሰላም ወደመጣበት የሚገባውን አሸኛኘት
ይድረግለታል።
Thursday, June 28, 2012
ምን እያለምን ነው?
በተለያዩ ዘመናት ራእይ አልባ ትውልዶች እንደነበሩ ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል።
ራእይ አልባ የሚባሉት ነገን አስበው ዛሬ መልካም ነገር ለማድረግ የማይተጉ። ወይንም ደግሞ ከዛሬ የተሻለ ነገን ተስፋ አድርገው
በመኖር በመከራ የማይታገሱ ናቸው። ለምሳሌ በሎጥ ዘመን የነበሩትን ትውልዶች ብንመለከት በሰዶም ከተማ ያሉ በሙሉ ከሊቅ እስከደቂቅ
በኃጢአት የተጨማለቁ ነበሩ። በመሆኑም ለነገ የሚተርፍ አንዳችም መልካም ስራ የሰሩት ስለሌለ ፍጻሜያቸው ጥፋት ሆነ። ለጊዜው እነሱን አነሳን እንጅ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን ከነሱ በፊትም ሆነ በኋላ በተለያየ ጊዜ ከህገ እግዚአብሔር ፈቀቅ ብለው በኃጢአታቸው ምክንያት አምላካቸውን ያስቆጡ ህዝቦች እንደነበሩ እንረዳለን። ዘፍ 6፥1 ዘፍ 11፥1 1ኛ ሳሙ 2፥31
Friday, March 30, 2012
ቆም ብሎ ማሰብ !
ሰውና እንስሳ ከሚለዩባቸው ነገሮች አንዱና ዋናው ነገር የሰው ልጅ የሚጠቅመውንና የማይጠቅመውን ለይቶ ማወቅ መቻሉ ሲሆን እንስሳት ግን ይህን የሚያውቁበት አእምሮ ስለሌላቸው በሰው ፈቃድና ፍላጎት ስር መሆናቸው ነው። ብዙ ጊዜ ረጋ ብሎ የሰሩት ነገር ፍሬያማ ይሆናል። የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል አደል የተባለው፥ ቀደም ሲል የነበሩት አባቶቻችን ሃገር ሲመሩ፣ ቤተክርስቲያንን ሲመሩ፣ ቤተሰብን ሲመሩ ቆም ብሎ የማሰብ ትልቅ ጸጋ ነበራቸው። ለዚያ ነው ዛሬም ድረስ ያ አሻራ ለትውልድ ተላልፎ ወደ ስህተት የሚጓዝን ሰው ቆም ብለህ አስብ ፣ ቆም ብለሽ አስቢ፣ ቆም ብላችሁ አስቡ እየተባለ በምሳሌ የሚነገረው።
Sunday, March 18, 2012
የዕለቱ ወንጌል
ማቴ 24፥1
1 ኢየሱስም ከመቅደስ ወጥቶ ሄደ፥ ደቀ መዛሙርቱም የመቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት ቀረቡ።
2 እርሱ ግን መልሶ። ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አላቸው።
3 እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው። ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።
4 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው። ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።
1 ኢየሱስም ከመቅደስ ወጥቶ ሄደ፥ ደቀ መዛሙርቱም የመቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት ቀረቡ።
2 እርሱ ግን መልሶ። ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አላቸው።
3 እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው። ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።
4 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው። ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።
Saturday, March 17, 2012
የእንጀራ ልጆች
በየትኛውም ማህበረሰብ ውስጥ ድርጊትን የሚያመለክቱ የተለያዩ የመገለጫ ቋንቋዎችን ወይንም ደግሞ ስሞችን እናገኛለን በእኛ ሀገርም ድርጊታዊ ሁኔታዎችን መሰረት ያደረጉ የተለያዩ ስሞችን እንጠቀማለን ከነዚህም አንዱ << የእንጀራ ልጅ >> የሚለው ነው።
የእንጀራ ልጅ ከስሙም እንደምንረዳው እውነተኛ ልጅ ያልሆነ እና እናት የተባለችውም የልጆች አባት የሆነ ባል ስላገባች እንዲሁም እንደወለደቻቸው ልጆቿ አድርጋ እንጀራ ስላበላች እንጅ ስለወለደች አይደለም ። የእንጀራ ልጅ ሁልጊዜ ለእንጀራ እናቱ የሚሰጣት ፍቅር በምታበላው እንጀራ ይወሰናል። እስኪጠግብ የበላ እለት እናቴ ይላታል አንድ ቀን የጎደለበት ጊዜ ግን ስሟን ማጥፋት ይጀምራል። ምክንያቱም ያገናኛቸው እንጀራ እንጅ በስጋ 9 ወር ከ 5 ቀን በማህጸኗ ተሸክማ አልወለደችውም። ከስጋዋ ስጋን ከነፍሷ ነፍስን የወሰደ ቢሆን ግን አካሉ ነችና ህመሟ ያመዋል፣ ደስታዋ ያስደስተዋል፣ ስሟ በክፉ ሲነሳ አይወድም፣ ከራሱ በላይ አብልጦ ይወዳታል። የእንጀራ ልጅ ግን ከሷ የተሻለ የምታበላው የምትንከባከበው ካገኘ ያችንም እናቴ ነሽ ይላታል። ነገር ግን አሁንም ጥቅሙ ከቀረበት ሌላ ፍለጋ መሄዱ አይቀርም ምክንያቱም መሰረታዊ ግንኙነታቸው ጥቅም ስለሆነ ማለት ነው። አንድ ኢትዮጵያዊ ምሁር በአንድ ወቅት የተናገሩትን አስታውሳለሁ << አንድ ሰው ለጥቅም ብሎ እግዚአብሔርን የሚያገለግል ከሆነ የተሻለ ጥቅም ካገኘ ሰይጣንንም ከማገልገል ወደኋላ አይልም ብለው ነበር >> ስጋዊ ጥቅም ከእግዚአብሔር መንግስት ይለያል። ሰው ደግሞ ከእግዚአብሔር መንግስት ከተለየ ሰው መባሉ ከንቱ ነው። በተለይ እንኳን የእግዚአብሔርን ቤት ለማገልገል የተመረጠ ይቅርና በክርስቶስ ክርስቲያን ተብሎ በስሙ የከበረ ሁሉ በስጋዊ ጥቅም መታለል አይገባውም። ይህን ስል በህይዎታችን የምናውቃቸው ብዙ መልካም ሰዎች ይኖራሉ ። የእናትን ውለታ ስለተረዱ ሴት ለተባለች ሁሉ ክብር የሚሰጡ፣ የእንጀራ እናታቸውን ከወለደቻቸው ልጆቿ አብልጠው የሚንከባከቡ እንዳሉ ባለመዘንጋት ነው። Wednesday, March 7, 2012
ስምና ተግባር
ስም( noun) መጠሪያ መለያ መገለጫ ወ , ዘ , ተ , ልንለው እንችላለን። በቀደመው ዘመን ስም ይሰጥ የነበረው ከተግባር ጋር ተያይዞ እንደነበር ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል ። በተለያየ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ከመልካም ስራቸው የተነሳ እግዚአብሔር አዲስ ስም የሰጣቸው ሰዎች እንዳሉም እናያለን። አብርሃምና ሳራ << ከዛሬም ጀምሮ እንግዲህ ስምህ አብራም ተብሎ አይጠራ፥ ነገር ግን ስምህ አብርሃም ይሆናል ለብዙ አሕዛብ አባት አድርጌሃለሁና። ዘፍ 17፥5 እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፦ የሚስትህን የሦራን ስም ሦራ ብለህ አትጥራ፥ ስምዋ ሣራ ይሆናል እንጂ። ዘፍ 17፥15 ፣ ያዕቆብ << እግዚአብሔርም፦ ስምህ ያዕቆብ ነው ከእንግዲህም ወዲህ ስምህ ያዕቆብ ተብሎ አይጠራ፥ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ አለ ስሙንም እስራኤል ብሎ ጠራው። ዘፍ 35፥10 >> ቅ/ጳውሎስ የሐዋ ሥ 13፥9፣ ቅ/ጴጥሮስ ማቴ 16፥6
ከእግዚአብሔር ቀጥሎ አዳም ለፍጥረታት ሁሉ መጠሪያ እንደሰጣቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፏል። ይህም ገዥነቱን አስተዳዳሪነቱን ያመለክታል። << እግዚአብሔር አምላክም የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ሁሉከመሬት አደረገ በምንስም እንደሚጠራቸውም ያይ ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው አዳምም ሕያው ነፍስ ላለው ሁሉ በስሙ እንደጠራው ስሙ ያው ሆነ። አዳምም ለእንስሳት ሁሉ፥ ለሰማይ ወፎችም ሁሉ፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ ስም አወጣላቸው ዘፍ 2፥19 >>
Monday, January 23, 2012
ይሉኝታ
በተነሳሁበት ርዕስ ዙሪያ ብዙ ጸሐፍያን እንደጻፉ፣ ወደፊትም እንደሚጽፉ እገምታለሁ። ነገር ግን ዛሬ ባለንበት ዘመን « ይሉኝታ » በብዙ ሰዎች ዘንድ የተዘነጋ በመሆኑ፣ አስፈላጊነቱንና አልፎ አልፎ ግን አላስፈላጊ የሚሆንበትም አጋጣሚ እንዳለ ለመጠቆም ያህል ነው። በተለይ ደግሞ በካህናት ዘንድ ከአስነዋሪ ተግባራት በስተቀር በይሉኝታ የምናልፋቸው ነገሮች ሊኖሩ እንደማይገባ በቅዱስ ወንጌሉ ተምረናል።ወንጌልንም ባልሰብክ ወዮልኝ ። 1ኛቆሮ 9፥16 ወንጌል ማለት ደግሞ እውነት ነው እንደጊዜው ሁኔታ እየተለዋወጡ የሚኖርበት አይደለም። ነገር ግን እግዚአብሔርን የማያስደስት ነገር ስንሰራ ሰውንም ሆነ እግዚአብሔርን ምን ይለኛል ማለት ይገባናል።
Saturday, January 21, 2012
ከእኔም ተማሩ
በቤተክርስቲያናችን በየዓመቱ ጥር 11 ቀን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጥምቀት ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ በታላቅ ድምቀት ይከበራል። በዓይነቱ ልዩ የሆነ በዓልም እናደርጋለን። ይህ ለምን ሆነ ብንል፣ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ የፈጸማቸው ነገሮች በሙሉ በቤተክርስቲያናችን ትርጉም ስላላቸው ነው። ሌሎችአብያተ ክርስቲያናት የጌታን በዮርዳኖስ በዮሐንስ እጅ መጠመቅ ከመናገር ያለፈ ትርጉም አይሰጡትም።
Wednesday, January 4, 2012
« መድኃኒነ ተወልደ ነዋ »
« መድኃኒታችን እነሆ ተወለደ »
የሰው ልጅ ለአምስት ሽ አምስት መቶ ዘመን በኃጢአት ደዌ በጸና ታሞ የሚፈውሰው መድኃኒት በማጣቱ በጨካኙ በዲያቢሎስ አገዛዝ ስር ወድቆ የፍዳና የኩነኔ ዓመታትን አሳልፏል። ተቆራኝቶት የነበረው ሰው ሊፈውሰው የማይችለው ደዌ ስለነበረ በየዘመኑ የተነሱ ጠቢባን ብዙ ቢደክሙም መድኃኒት ማግኘት ግን አልቻሉም ነበር።
ቢሆንም ግን የተያዘበት በሽታ ባለመድኃኒቱ እስኪገለጥ ድረስ ቢያሰቃየውም ፈጽሞ እንዲያጠፋው የፈጣሪው ፈቃድ አልነበረምና ያንን መድኃኒት በየዘመኑ የነበሩት አበው ተስፋ ባለመቁረጥ ሲጠብቁ ኖረዋል። « እግዚአብሔር ሆይ፥ መድኃኒትህን እጠብቃለሁ። ዘፍ 49፥18
Sunday, January 1, 2012
መንጋውን ለሚተው ለምናምንቴ እረኛ ወዮለት! ት,ዘካ 11፥17
ዛሬ እለቱ ታህሳስ 22/ 2004 ዓ/ም ሲሆን እንደ ቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ በዚህ እለት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የመጽነሷን ዜና የነገረበት እለት ነው። ከዚሁም ጋር እለቱ እለተሰንበት ላይ ስለዋለ ድርብ በዓል ነው። ታላቁ የቤተክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ ያሬድ የዛሬውን ሰንበት ኖላዊ ወይንም ደግሞ መልካም እረኛ የሚል ስም ሰጥቶታል። ያለፉት ሁለት ሳምንታት እና የዛሬው ሰንበት የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ከድንግል ማርኃም በስጋ መወለድ እያሰብን የልደቱን ብርሃን ለማየት በተስፋ ደጅ የምንጠናበት ነው።
Subscribe to:
Posts (Atom)