አትናወጡ ጽኑ በእምነት
ብሎ አረጋጋ በሰማያት
ገብርኤል ሊቀ መላእክት
ሳጥናኤል ክዶ ቦሳሳት
አላምንም ብሎ በትእቢት
የፈጠረንን እስክናውቅ
ጽኑ አለ ገብርኤል እንጠብቅ
አዝ,,,,,,,
በቅድመ እግዚአብሔር የሚቆመው
ስለኛ መዳን የሚተጋው
በቀን በሌሊት ጠባቂያችን
ቅዱስ ገብርኤል ረዳታች
አዝ,,,,,,,
የድህነት ዜናን የሰበከ
በእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ
ሆነ ለነፍሳችን ጠበቃ
ገብርኤል የመላእክት አለቃ
አዝ,,,,,,
የእሳቱን ዋእይ አጠፋልን
የወይኑን ደጃፍ ከፈተልን
ከፊታችን ነው ገብርኤል
ሞገዱን አለፍን ማእበሉን
አዝ,,,,,,,,,
ብሎ አረጋጋ በሰማያት
ገብርኤል ሊቀ መላእክት
ሳጥናኤል ክዶ ቦሳሳት
አላምንም ብሎ በትእቢት
የፈጠረንን እስክናውቅ
ጽኑ አለ ገብርኤል እንጠብቅ
አዝ,,,,,,,
በቅድመ እግዚአብሔር የሚቆመው
ስለኛ መዳን የሚተጋው
በቀን በሌሊት ጠባቂያችን
ቅዱስ ገብርኤል ረዳታች
አዝ,,,,,,,
የድህነት ዜናን የሰበከ
በእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ
ሆነ ለነፍሳችን ጠበቃ
ገብርኤል የመላእክት አለቃ
አዝ,,,,,,
የእሳቱን ዋእይ አጠፋልን
የወይኑን ደጃፍ ከፈተልን
ከፊታችን ነው ገብርኤል
ሞገዱን አለፍን ማእበሉን
አዝ,,,,,,,,,
ሆነችን ማርያም እናታችን
እናቱ የጌታችን ለምኝ ለሁላችን
ይቅር እንዲለን እንዲታረቀን
ያሳየን መህረቱን በላያችን
ሰራልን ሰንበትን ለእረፍታችን
ደስታ ሆነልን ለምናምን
ሰራልን ሰንበትን ለእረፍታችን (2)
ደስታ ሰላም ሆነልን ለምናምን (2)
ለትውልድ የሚነገር ክብርሽ
ለልጅ ልጅ የሚታሰብ ስራሽ
ማርያም ድንግል ንጽህት ነሽ
ማርያም ድንግል ብጽእት ነሽ
.....,..........
ቅድመ ዓለም ታስበሽ በህሊና
በመቅደሱ ኖረሽ በትህትና
አደረገሽ ማደሪያው ዘላለም
ከፍጥረቱ የሚመስልሽ የለም
አዝ.......
ብርሃንን የወለድሽ ብርሃን
ምክንያት ነሽ ለዓለሙ መዳን
ካንች ወጣ የምስራቁ ፀኃይ
ማታው አልፎ ብርሃንን እንድናይ
አዝ........
ትውልደ ካም ትውልደ ሴም ያፌት
ያቀርባሉ የምስጋና መስዋእት
ተሞልተዋል በቅዱስ መንፈሱ
የአምላክ እናት ብለው ሲያወድሱ
አዝ......
በዐቢይ ቃል ብጽእት ብንልሽ
ከእግሮችሽ ስር ብንወድቅልሽ
ከሰማያት ስምሽን ተምረን ነው
ሰዓሉ ለነ ቅድስት የምንለው
አዝ....
ሳወድስሽ ልኑር ጸጋው በዝቶልኝ
ማርያም ሆይ ለስምሽ ምስጋና አለኝ
ድንግል ሆይ ለክብርሽ ውዳሴ አለኝ
የህይወት የነየነጻነት ሰሌዳ
እንዲፋቅ የአዳም ልጆች እዳ
ፈለቀ ከሆድሽ መድኃኒት
ሊሊያድነን ወደደን እስከሞት (2)
አዝ,,,,,
ኃዘኔን የረሳሁብሽ ደስትደስታ
ለጥሜ የሆንሽልኝ እርካታ
ወልደሽው የህይወትን እንጀራ
ቆሜያለሁ ከቅዱሱ ተራራ (2)
ጎጆየን በረከት ያስሞላሽ
ድካሜን ጉድለቴን የሸፈንሽ
ጣፈጠ የመረረው ህይዎቴ
እመአምላክ ሆነሽልኝ ሙላቴ (2)
አዝ......
ስላንች ተቀበለ ጸሎቴን
በምልጃሽ ፈጸመልኝ መሻቴን
አይኖቼ ወደላይ ያቀናሉ
ድንግል ሆይ ለምኝልን ይላሉ (2)
የሚያዝኑ ብጹዓን ናቸው (2)
ያገኛሉ መጽናናትን(2)
አዳም በኃጢአቱ ከገነት ሲወጣ
እንባ ነበር ለርሱ የቀረለት እጣ
እንደ ክረምት ውሃ ፈሰሰ ከዓይኑ
ስለዚህ አዳነው ኢየሱስ መድህኑ(2)
አዝ.....
ዳዊት በኦርዮ ግፍ በሰራ ጊዜ
በእንባው ታጠበ የልቡ ትካዜ
ነቢዩ ናታንም አጥብቆ ገሰጸው
ዳዊትም ማቅ ለብሶ አምላኩን ለመነው(2)
አዝ....
ጴጥሮስ አሣ ሊያጠምድ እሄዳለሁ አለ
ጌታው በቀራንዮ ተሰቅሎ ስላየ
ጥብርያዶስ ባህር ጌታ ሲገለጽ ግን
እጅግ ጥልቅ ነበር የልቦናው ሃዘን(2)
በገዛ ደሙ የዋጃትን
የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን
ትጠብቁ ዘንድ እናንተን የሾማችሁ
ተጠንቀቁ ለመንጋውና ለራሳችሁ
መንፈስ ቅዱስ አፍ አድርጓችኋል
በህዝቡ ላይ አሰልጥኗችኋል
ዓይኔ ናችሁ ብሏችኋልና
ልኳችኋል ህዝቡ እንዲጽናና (2)
አዝ.......
እንድታስሩ ደግሞም እንድትፈቱ
ደካማውን እንድታበረቱ
ለመንጋው ሁሉ ምሳሌ እንድትሆኑ
እንዲገለጥ በእናንተ ማዳኑ (2)
አዝ....
በጾምና በጸሎት ተግታችሁ
በቁስሉ ላይ ዘይት አፍስሳችሁ
ብኩርናውን ስለጌታ ናቁ
በፍቅር ሁኑ ስለ ጽድቅ ንቁ (2)
አዝ....
እኔ የኬፋ ደግሞም የአጵሎስ
አትበሉ የጴጥሮስ የጳውሎስ
አንድ እምነት ነው አንድ ነው ጥምቀት
አንድ ስልጣን አንድ ነው እርስት (2)
በእግዚአብሔር ፊት ታምኖ
በተሰጠው ጸጋ በአገልግሎት ተግቶ
የተገኘው ባሪያ ታማኝ ሰለሆነ
በጌታው ተወዶ በብዙ ታመነ (2)
አምስቱን ሁለቱን አብዝቶ ጠበቀው
ምንሰራህ እያለ ጌታው ሲጠይቀው
መክሊቱን ባደራ መጠበቁ ሳያንስ
እጅግ ያስደንቃል አብዝቶ ሲመልስ
አዝ.....
አንዱ ቅንጣት ስሳ መቶ ስላፈራ
ይደሰት ተባለ ከመላእክት ጋራ
ጎተራው በፍሬ ተሞልቶ ቢያገኘው
ባሪያውን ተደሰት ከእኔ ጋር አለው
አዝ....
ሞፈር ተሸክመው ይጓዛሉ ሊያርሱ
በሰማዩ ዝናብ በጭቃው ሲያለቅሱ
ሲመለሱ ዘርተው ደክመው ተጎሳቁለው
ይስቃሉ ፍጹም ነዶ ተሸክመው
አዝ...