ዛሬ ስላለንበት ዘመን ስንናገር ምናልባትም ማንም የማይቀማንን ሙሉ መብት ተጠቅመን በልበ ሙሉነት መናገር እንችላለን። ምክንያቱም ክፉም ይሁን በጎ ዘመኑ እኛ የተፈጠርንበት በመሆኑ የኛ ዘመን ነው ብሎ ለመናገር ፈቃድ አያስፈልገውም። አንድን ነገር የኔ ነው ለማለት በህግ ፊት የሚቀርብ የባለቤትነት ማስረጃ ያስፈልጋል።እናም የኛ ማስረጃ በዚህ ዘመን መፈጠራችን ብቻ ነው።
Saturday, December 31, 2011
Thursday, December 29, 2011
እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ ሉቃ 1፥19
ዛሬ በሃገራችን በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ዘንድ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል የሚታሰብበት እለት ነው። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል በዛሬው እለት ሠለስቱ ደቂቅን ( ሶስቱን ወጣቶች ) ከእሳት ያወጣበት እለት ነው። የቤተክርስቲያን አባቶች ሊቃውንት ዓመቱን በሙሉ እግዚአብሔርን እናከብር ዘንድ በተለያየ ጊዜ በቅዱሳኑ ላይ አድሮ ያደረገውን ታላላቅ ተዓምራት እናስብ ዘንድ እለታቱን በሙሉ እግዚአብሔርን እንድናመሰግንባቸው ስርዓትን ሰርተውልናል።
Monday, December 26, 2011
በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ ኢሳ 9፥2
የዛሬው ሰንበት እንደቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ብርሃን ይባላል። ስያሜው የተሰጠው በቅዱስ ያሬድ ሲሆን ወቅቱም የጌታን መወለድ በተስፋ ይጠባበቁ የነበሩት የአዳምና የልጆቹን ደጅ ጥናትን የምናስታውስበት ነው። በመሆኑም ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ፈኑ ብርሃነከ ወጽድቀከ እማንቱ ይምርሃኒ ( ብርሃንህንና እውነትህን ላክ እነርሱ ይምሩኝ። መዝ 43፥3) ብሎ ተናግሯል። ስለሆነም ቤተክርስቲያናችን የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት አስቀድማ ለልጆቿ ጾም ጸሎት እያደረጉ ደጅ እንዲጠኑ ታዛለች።
የሰው ልጅ የፈጣሪውን ትእዛዝ በማፍረሱ ምክንያት ለ5500 ዘመን በዲያቢሎስ ባርነት ተይዞ በጨለማ አገዛዝ ስር ወድቆ ይኖር ነበር። ይሁን እንጅ እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጅ ደካማ በመሆኑ በዲያቢሎስ ክፉ ምክር ተታሎ እንደወደቀ ያውቅ ነበርና ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ የሚለውን የተስፋ ቃል ነግሮት ነበር። በመሆኑም እስከ ዘመኑ ፍጻሜ ድረስ አዳምና ከእርሱ በኋላ የነበሩት ልጆቹ በሞተ ስጋ ላይ ሞተ ነፍስ ተጭኗቸው በሲኦል በዲያቢሎስ ተረግጠው ይኖሩ ነበር።

Saturday, December 17, 2011
ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን
<< ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሰላም ጸልዩ >>
ሁልጊዜ በስርዓተ ቅዳሴያችን ላይ የሚነገር አዋጅ ነው። በሰው ዘንድ በተደጋጋሚ የሚነገር ነገር ብዙ ጊዜ ክብርና ቦታ አይሰጠውም ስለዚያም ይመስላል ብዙ ሰው ይህ አዋጅ ሲታወጅ የተለመደ ስለሆነ ብቻ የዲያቆኑ የአገልግሎት ድርሻ መሆኑን ከመገመት ያለፈ ቦታ የማንሰጠው።
ሁልጊዜ በስርዓተ ቅዳሴያችን ላይ የሚነገር አዋጅ ነው። በሰው ዘንድ በተደጋጋሚ የሚነገር ነገር ብዙ ጊዜ ክብርና ቦታ አይሰጠውም ስለዚያም ይመስላል ብዙ ሰው ይህ አዋጅ ሲታወጅ የተለመደ ስለሆነ ብቻ የዲያቆኑ የአገልግሎት ድርሻ መሆኑን ከመገመት ያለፈ ቦታ የማንሰጠው።
Tuesday, August 16, 2011
እንደ ተቀማም አልቆጠረውም
ሰዎች አንድን ነገር ብንሰርቅ ወይም በጉልበት መንትፈን ብንወስድ ሌሎች እንዳይወስዱብን እንደብቀዋለን፤ አሊያም በጥንቃቄ እንይዘዋለን፡፡ ወደ ሥልጣን ከወጣን በኋላም መልሰን ወደ ታች መውረድ እንፈራለን፡፡ ብንወርድ እንኳን ታጅበን እንሄዳለን፡፡ ጉዞአችንም ሁሉ በፍርሃት የተመላ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም የተቀመጥንበት ወንበር ከመጀመርያውኑ የእኛ ሳይሆን ሌሎች ነበሩበትና፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የባርያዎቹን መልክ ይዞ ከልዕልና ወደ ትሕትና ወረደ፡፡ ሲመጣም ብቻውን መጣ እንጂ በመላእክት ወይም በሌላ ጭፍራ አልተጠበቀም፡፡ ሰው ሆኖ ራሱን ባዶ ስላደረገም ከአባቱ ጋር ያለውን መተካከል አላስቀረበትም፤ እንደ ተቀማም አልቆጠረውም፡፡ ማንም አይወስድበትና “የባርያዎቼን መልክ አልይዝም” ብሎም አልተከራከረም፡፡ የማዳን ሥራውን ከፈጸመ በኋላ ዓለም ሳይፈጠር ከአባቱ ጋር በነበረው ክብር የሚቀመጥ አምላክ ነውና፡፡ ይህ ሥልጣኑ ድሮውንም የባሕርዩ ነውና ራሱን ዝቅ ዝቅ አደረገ፤ ለሞት ይኸውም ለመስቀል ሞት እንኳን የታዘዘ ሆነ፡፡
ሞታችንን ለሞተልን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁንለት፤ አሜን፡፡
ሞታችንን ለሞተልን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁንለት፤ አሜን፡፡
Sunday, August 7, 2011
የሃይማኖት ጉዞ
የሃይማኖትን ጉዞ በማስፈረራራት ማስቆም አይቻልም !!!ዘመኑ ሃሰት የነገሠበት ዲያቢሎስ የሰለጠነበት ሁኗል :: እውነተኛ ክርስቲያኖች ሊሳደዱ ሊገፉ አግልግሎታቸው ሊደናቀፍ የሌለባቸው ክፉ ስም ሊሰጣቸው ይችል ይሆናል፤ ይህን ደግሞ ጌታችን “ ስለ ስሜ በአህዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ “ ማቴ ፳፬፥፱
በማለት እንደተናገረ በጎ እያደረግን ስለስሙ ስንነቀፍ ስንሳደድ ስንጠላ ደስ ሊለን ይገባል :: የተጠራነው ለዚህ ስለሆነ ጥርጥር በሌለበት ሃይማኖት ልንጸናም ያስፈልጋል ::
ቅዱስ ያዕቆብ “ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደሙሉ ደስታ ቁጠሩት :: ” ያዕ ፩፥፪ እንዳለ ስለ እግዚአብሔር ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ብንፈተን ዋጋ ያለው መሆኑን እንወቅ ::ፈተና ፦በእውነት እግዚአብሔርን እያገለገልን ከመጣ የምንደሰትበት እንጅ የምናዝንበት አለመሆኑን የእውነት ተጻራሪ ለሆኑ ሁሉ ማሳየት ተገቢ ነው :: ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ብንነቀፍ ከኛ ጋር ያለው እግዚአብሔር ከሁሉም በላይ ነውና አንሸበርም :: እግዚአብሔርን ሊያሸንፍ የሚችል ማንም የለምና :: “ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቅቃሉ::” ፩ኛ ሳሙ ፪፥፲ ሥራውንም ማስተጓጎል አይቻልም ደግሜ እላለሁ ፡ በእውነት የሃይማኖትን ጉዞ በማስፈረራራት ማስቆም አይቻልም !!!

Friday, August 5, 2011
የሚያዝኑ ብጹዓን ናቸው
ዛሬ የሚያዝኑና የሚያለቅሱ የተመሰገኑ ናቸው፣ መጽናናትን ያገኛሉና» /ማቴ 5÷4
ዕንባ የተጀመረው በአዳምና በሔዋን ነው፡፡ ያለቀሱትም አትብሉ የተባሉትን ዕፀ በለስ በልተው እግዚአብሔርን በመበደላቸው ምክንያት ነው፡፡ ስለዚህ ዕንባ የተጀመረው በንስሐ ነው፡፡ በቀሌምንጦስ «አልቦቱ ካልዕ ሕሊና ለአዳም ዘእንበለ ብካይ ላዕለ ኃጢአቱ፤ ለአዳም ስለ ኃጢአቱ ከማልቀስ /ኃጢአቱን እያሰበ ከማልቀስ/ በቀር ሌላ አሳብ /ግዳጅ/ አልነበረውም» ተብሎ እንደተጻፈ፡፡ የዕንባ ቀዳሚ ጠቀሜታ ሰውን በንስሐ ከእግዚአብሔር ጋር ማስታረቅ ነው፡፡ ይህም በመጽሐፍ ቅዱስ ተደጋግሞ ተመዝግቧል፡፡ «ወበአንብዕየ አርሐስኩ ምስካብዬ፤ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ» የሚለው ቅዱስ ዳዊት የንስሐ ዕንባውን፣ የጸሎት ዕንባውን ነው፡፡ /መዝ 6÷6/ ጌታችንም በወንጌል «ብፁዓን እለ ይላህው ይእዜ እስመ እሙንቱ ይትፌስሑ፤ ዛሬ የሚያዝኑና የሚያለቅሱ የተመሰገኑ ናቸው፣ መጽናናትን ያገኛሉና» /ማቴ 5÷4/ ሲል ያስተማረው የሚገባው ለቅሶ ወይም ዕንባና ሐዘን የንስሐ መሆኑን ያስረዳናል፡፡ በሌላም ቦታ «እናንተ አሁን የምትስቁ ወዮላችሁ፣ ታዘናላችሁና፣ ታለቅሱማላችሁ» /ሉቃ 6÷25/ ሲል ያስጠነቀቀን ጠቃሚውን ዕንባና ሐዘን ለማስተማር ነው፡፡ መፍቀሬ ጥበብ ሰሎሞንም «ከሳቅ ሐዘን ይሻላል፣ ከፊት ኀዘን የተነሣ ደስ ይሰኛልና፤ የጠቢባን ልብ በልቅሶ ቤት [በንስሐ] ነው፤ የሰነፎች ልብ ግን በደስታ ቤት [ኃጢአት በሚፈጸምበት ቦታ] ነው» በማለት የንስሐ ዕንባን መፈለግ ጠቢብነት እንደሆነ ይነግረናል፡፡ከዚህም በላይ በቅድስና ሕይወት የሚኖሩ ቅዱሳን በዐሥሩ መዓርጋት ሲሸጋገሩ አራተኛው መዓርግ አንብዕ ይባላል፡፡ ይህም ፊታቸው ሳይከፋውና ሰውነታቸው ሳይሰቀቅ ዕንባን ከዓይናቸው ማፍሰስ ነው፡፡ ስለዚህ ዕንባ ይህን የመሰለ ጠቀሜታ ያለው በመንፈሳዊነትም የብቃት ደረጃ ሆኖ እናገኘዋለን ማለት ነው፡፡
Saturday, July 2, 2011
የባርነታችሁን ቀንበር ሰብሬያለሁ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
ባሪያዎች እዳትሆኑአቸው ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ የባርነታችሁን ቀንበር ሰብሬአለሁ ቀና ብላችሁ እንድትሄዱ አድርጌአችኋለሁ። ዘሌ 26፥13
ይህንን ቃል የተናገረው እግዚአብሔር አምላካችን በባሪያው በሊቀ ነቢያት ሙሴ አማካኝነት ነው እስራኤላውያን በግብጽ ባርነት ለ400 ዓመት ከቆዩ በኋላ መከራው ስለጸናባቸው ወደ እግዚአብሔር ጮሁ እግዚአብሔርም ጩኸታቸውን ሰምቶ በሊቀ ነቢያት ሙሴ አማካኝነት ታላላቅ ተአምራትን አድርጎ ከግብጽ ምድር አወጣቸው በግብጽ በረሃ ከዓለት ላይ ውሃ እያፈለቀ ከደመና መና እያወረደ እየመገበ ወደ ተስፋይቱ ምድር ጉዞ ጀምረው ነበረ ይሁን እንጅ ህዝበ እስራኤል እግዚአብሔር ያደረገላቸውን ውለታ በመዘንጋት ወደ ጣኦት አምልኮ ፊታቸውን በማዞራቸው እግዚአብሔር ተቆጥቷቸዋል

Friday, July 1, 2011
የዘላለም ሕይዎት
የዘላለም ህይዎትን እንድዎርስ ምን ላድርግ ?
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳም የገባውን ቃል ሊፈጽም ሰው በሆነበት ዘመን በሰፊው ያስተምር የነበረው የዘለዓለም ህይወትን ሊሰጥ እንደመጣ ነበር። ነገር ግን ብዙዎች የቃሉን ትምህርት የእጁን ተአምራት እያዩ ቢያምኑበትም እስከ መጨረሻው የተከተሉት ጥቂቶች ነበሩ። ስለ ዘላለም ህይወት አራቱም ወንጌላውያን በሰፊው ጽፈዋል። ወንጌላዊው ሉቃስ የጻፈውን እናስቀድም ,, ከአለቆችም አንዱ። ቸር መምህር፥ የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ? ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስም፦ ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም። ትእዛዛቱን ታውቃለህ፥ አታመንዝር፥ አትግደል፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥ አባትህንና እናትህን አክብር አለው። እርሱም፦ ይህን ሁሉ ከሕፃንናቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ አለ። ኢየሱስም ይህን ሰምቶ። አንዲት ገና ቀርታሃለች፤ ያለህን ሁሉ ሽጠህ ለድሆች ስጥ፥ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ አለው። እርሱ ግን ይህን ሰምቶ እጅግ ባለ ጠጋ ነበርና ብዙ አዘነ። ኢየሱስም ብዙ እንዳዘነ አይቶ። ገንዘብ ላላቸው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ይሆናል። ባለ ጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ሊገባ ይቀላል አለ። ሉቃ 18፥18
Subscribe to:
Posts (Atom)