ሃብታም ሃገራት ስደተኞችን የሚቀበሉበት መስፈርት በራሱ ፖለቲካዊ ብቻ
ነው። አንድ ሰው ተርቦ እሚበላው አጥቶ ከሃገር ቢሰደድ መስፈርቱን አላሟላህም ተብሎ ተቀባይነት አያገኝም። ነገር ግን ሌላው በሃገሩ
ላይ ወንጀል ሰርቶ ወይንም በመንግስት ላይ አምጾ ከቀረበ የስደተኛ መብት ያገኛል። የሚቀርበው ምክንያት ደግሞ ሃገሩ ቢመለስ ሊታሰር ይችላል የሚል ነው፤ ይህ መሆኑ ባልከፋ ነገር ግን ረሃብ ለስደት በቂ ምክንያት አይደለም መባሉ ሊፈተሽ የሚገባው ጉዳይ ነው። ረሃብ የሚመጣው ከበስተጀርባው ባሉ ብዙ ወንጀሎች ምክንያት ነው።ለኢኮኖሚ ስደተኞች መጠጊያ የለንም የሚሉ ሃገራት ብዙ ናቸው። ይህ ስደት የሚለውን ትርጉም ያዛባ ውሳኔ መሆኑን
ለመረዳት ስደት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ማወቅን ይጠይቃል።
Monday, July 20, 2015
Tuesday, July 14, 2015
ስደት በኛ ዘመን
ለስደት ስናነሳ ከመሰረቱ ማየት ያስፈልጋል። ከሃይማኖታችን አንጻር ስናየው
ስደት ሁለት ዓይነት ነው። በነፍስ የሚገጥመን ስደትና የስጋ ስደት ማለት ነው። የስደት ጀማሪዎች አባታችን አዳምና እናታችን ሄዋን ናቸው። (ዘፍ 3፥23)
የነሱ ስደት የነፍስና የስጋ ስደት ይባላል። በህይወተ ስጋ ሳሉ ከገነት
ወደ ምድረ ፋይድ ተሰደዋል። ከሞቱም በኋላ በነፍስ ወደ ሲኦል መሰደድ ግድ ሆኖባቸዋል።
ክፉው ስደት የነፍስ ስደት ነው። አባታችን አዳም በምድራዊ ስደት የኖረው
923 ዓመት ሲሆን በገነት ለ7 ዓመታት ብቻ እንደኖረ ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል። በነፍሱ ደግሞ ከነልጆቹ ለ5500 ዘመናት በስደት
ኖሯል። ለመኖሪያነት ከተሰጠችው ከመጀመሪያ ሃገሩ ከምድረ ገነት ሰይጣን ዲያቢሎስ በሸረበበት ተንኮል ምክንያት ስደት አግኝቶታል።
አስቀድሞ እግዚአብሔር ወደ ቀደመ ርስቱ እንደሚመልሰው ቃል ገብቶለት ስለነበር ጊዜው ሲደርስ ወደ ገነት መልሶታል።
Tuesday, July 7, 2015
የሰው ልጅ መብት የት ድረስ ነው?
እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ሲፈጥረው አእምሮ የሚባል ዳኛ ህግ የሚባል
ልጓም ስጥቶታል። ይህም ያስፈለገበት ምክንያት ሰው ለክብር የተፈጠረ ስለሆነ ስሙን ለመቀደስ ክብሩን ለመውረስ ይችል ዘንድ ነው።
ህሊና እና ህግ ያልተሰጣቸው እንስሳት ከሞት በኋላ ያለውን ክብር ስለማይወርሱ እንዲጠብቁ የታዘዙት ህግ የለም። በህግ መመራት በነፍስም
በስጋም የሚጠቅመው ሰውን ነው። ያለ ህግ መኖር እንስሳዊ ባህርይን
መላበስ ነው። በህግ ጥላ ስር ስንኖር እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ይኖራል። ህግ የተሰራላቸው ህዝበ እግዚአብሔር እስራኤል ከእግዚአብሔር
ህግ ፈቀቅ ባሉ ጊዜ ይደርስባቸው የነበረውን መከራና ችግር ቅዱስ መፅሐፍ በሰፊው ይነግረናል። የእግዚአብሔር መንፈስ አድሮበት የተናገረው
አዛርያስ እንዲህ ብሏል >> አሳ ይሁዳና ብንያም
ሁሉ ሆይ፥
ስሙኝ እናንተ
ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆኑ
እርሱ ከእናንተ
ጋር ነው
ብትፈልጉትም ይገኝላችኋል ብትተዉት
ግን ይተዋችኋል
<< 2ኛ ዜና 15፥2 ይህን ያላቸው ከህገ እግዚአብሔር ርቀው ስለነበር እግዚአብሔርም ርቋቸው ስለነበር ነው። ይህንንም
ከዚሁ ምእራፍና ቁጥር ቀጥሎ እንዲህ ተጽፎ እናነበዋለን >>
እስራኤልም
ብዙ ዘመን
ያለ እውነተኛ
አምላክ፥ ያለ አስተማሪም
ካህን፥ ያለ ሕግም
ይኖሩ ነበር። በመከራቸውም
ወደ እስራኤል
አምላክ ወደ እግዚአብሔር
ተመልሰው በፈለጉት ጊዜ
አገኙት። በዚያም ዘመን ለሚወጣውና
ለሚገባው ሰላም አልነበረም፥
በምድርም በሚኖሩት ሁሉ
ላይ ታላቅ
ድንጋጤ ነበረ << ይላል ስለዚህ ሰዎች ከእውነተኛው
ከእግዚአብሔር ህግ ከወጡ ፍርሃትና ጭንቀት ችግርና መከራ ያገኛቸዋል። ይህም በመሆኑ የተነሳ እግዚአብሔር በየዘመኑ ህጉን የሚያስፈጽሙ
መሪዎችን እና አስተማሪዎችን ከህዝቡ መካከል እያስነሳ ህዝቡን ይመራል ያስተምራል።
Saturday, May 9, 2015
አውሬ ማለት . . . . . . . . .?
ከፍጥረታት መካከል ሰውና እንስሳት ከድርጊት ጋር በተያያዘ የሚሰጣቸው ስም አለ። ያ ስም ቀድሞ የተሰጣቸው ሳይሆን በኋላ
ከተፈጥሯዊ ጠባያቸው ወጣ ባለ መንግድ ድርጊትን ሲፈጽሙ በመገኘታቸው ነው። የሰውን ብንመለከት በመልካም ሰዎች የተነሳ ለእግዚአብሔር
ልንሰጠው የሚገባውን የአክብሮት ስያሜ ለሰዎች እንሰጣለን። ለምሳሌ ቸር፣ ሩህሩህ፣ ለጋስ ፤ትሁት፤ቅን ,,,,,,,, ወዘተ በተቃራኒው ደግሞ ለዲያቢሎስ ልንሰጠው የሚገባውን ስያሜ ለሰዎች የምንሰጥበት
ጊዜ አለ ምክንያቱም በግብር ስለሚመስሉት ነው። ለምሳሌ ክፉ፣ ጨካኝ ፣ አረመኔ፣ ነፍሰ ገዳይ፣ አውሬ , , , , , ወዘተ ልንል
እንችላለን።
Subscribe to:
Posts (Atom)