ከፍጥረታት መካከል ሰውና እንስሳት ከድርጊት ጋር በተያያዘ የሚሰጣቸው ስም አለ። ያ ስም ቀድሞ የተሰጣቸው ሳይሆን በኋላ
ከተፈጥሯዊ ጠባያቸው ወጣ ባለ መንግድ ድርጊትን ሲፈጽሙ በመገኘታቸው ነው። የሰውን ብንመለከት በመልካም ሰዎች የተነሳ ለእግዚአብሔር
ልንሰጠው የሚገባውን የአክብሮት ስያሜ ለሰዎች እንሰጣለን። ለምሳሌ ቸር፣ ሩህሩህ፣ ለጋስ ፤ትሁት፤ቅን ,,,,,,,, ወዘተ በተቃራኒው ደግሞ ለዲያቢሎስ ልንሰጠው የሚገባውን ስያሜ ለሰዎች የምንሰጥበት
ጊዜ አለ ምክንያቱም በግብር ስለሚመስሉት ነው። ለምሳሌ ክፉ፣ ጨካኝ ፣ አረመኔ፣ ነፍሰ ገዳይ፣ አውሬ , , , , , ወዘተ ልንል
እንችላለን። በተለይ አውሬ የሚለውን ስያሜ ለሰውም ለእንስሳም ልንጠቀመው እንችላለን። አውሬ የሚለው የግብር ስም ነው። ብዙዎቻችን
አውሬ የምናውቀው በጫካ እሚኖር፣ አድኖ የእለት ጉርሱን የሚያገኝ ከእንስሳት ወገን የሆነ ፍጥረትን ነው። እውነቱ ግን ይህ አይደለም።
ከሰውም ከመላእክትም ከእንስሳትም አውሬ አለ። የመጀመሪያው አውሬ ከመላእክት ወገን የሆነው ሰይጣን ዲያብሎስ ነው። ራዕ 10፥20 --17፥8 ከዚያም የሰው
ልጆች በግብር ስለመሰሉት አውሬ ሆነው የተገኙ አሉ። ራዕ 17፥3
አሁን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ስናየው የሰው አውሬዎች እየበረከቱ ሲሆን በተቃራኒው እንስሳት ለሰው የተሰጠውን ጸጋ
ርህራሄ፣ምህረት፣ቸርነት እየወሰዱ ነው። የሰው አውሬነት ዘርፈ ብዙ ነው። ገንዘብን በመውደድ የሚመጣ አለ። ከጭካኔ የሚመጣ አለ.
እንዲሁም ከጥላቻ የሚመነጭ አለ። እንዚህ ሁሉ ዲያቢሎስ ለሰው ልጆች ያወረሳቸው ናቸው። በዓለማችን ውስጥ አደገኛ አውሬ ተብለው
በሰው ልጆች ዘንድ የሚጠሩት እንስሳት ዛሬ ሰውን አገልጋይና ተንከባካቢ እየሆኑ መጥተዋል። ስለዚህ የነሱን ስራ የሚሰራለት ዲያቢሎስ
ያስፈልገዋል። በዚህም የተነሳ የሰውን ልጆች መሳሪያ እያደረገ ይገኛል። ስለዚህ አሁን ማደን ያለብን የእንስሳት ወገን የሆኑ አውሬዎችን
ሳይሆን የሰው አውሬዎችን ነው። ይገደሉ፣ እነሱ በሌላው ላይ እንዳደረጉት አሰቃቂ ድርጊት ይፈጸምባቸው ባይባልም አውሬ ግን መታሰር
አለበት። ከዚህ ባህሪው እስኪስተካከል ድረስ ከሰው መቀላቀል አይገባውም።
በአሁኑ ወቅት የምንሰማው ዜና በሙሉ ህሊናን የሚያደማ፣ አእምሮ ካለው የሰው ልጅ የማይጠበቅ አሰቃቂ ድርጊት እየተፈጸመ
መሆኑን ነው። በተለይ በክርስቲያኖች ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይና መከራ በርትቷል። ይሁን እንጅ ይህ ስቃይና መከራ እንዴት መቆም
እንዳለበት እየሰራን ያለን አይመስልም። ወገኖቻችን ኢትዮጵያውያን በስደት ሃገር እየደረሰባቸው ያለው እንግልት የመላው ዓለምን ህዝብ
እያነጋገረ ነው። የዚህ ሁሉ ችግር መነሻው ይታወቃል። የአውሬ እራት የሚሆን መንጋ ምክንያቱ እረኛው ተኝቷል ወይም ታስሯል ወይም
ደግሞ በህይወት የለም ስለዚህ የተኛውም ሊነቃ ይገባዋል። የታሰረውም ሊፈታ ይገባዋል። በሞተውም እውነተኛ እረኛ እግዚአብሔር እንዲሰጥ
መጸለይ ይገባል።
ለዓለማችን ከፍተኛ ስጋት ሆኖ ብቅ ያለው isis የተባለው የአውሬ መንጋ እንደተለመደው በወገኖቻችን ላይ አረመኔያዊ
ድርጊት ሲፈጽም የሚያሳይ VIDEO በመላው ዓለም ተለቆ ህዝብ እየተመለከተው ነው። ይህ ነገር ተደጋጋሚ ከመሆኑ የተነሳ የዓለም
መንግስታት ወደ እርምጃ ከመሄድ ይልቅ በየእለቱ የሱን የተለያየ አረመኔያዊ ተግባራት በየሚዲያቸው በማንጸባረቅ ገንዘብ መሰብሰቢያ እያደረጉት እንደሆነ በግልጽ እየታየ ነው። እርግጥ ነው
በዓለም ውስጥ ይህን አረመኔያዊ ተግባር የሚደግፉ ህዝቦችና መንግስታት ይኖራሉ ተብሎ ይታመናል። ምክንያቱም ይህን ያክል የተደራጀው
በኃይል ብቻ ሳይሆን ስውር ዓላማ ካላቸው አካላት በሚደረግለት ድጋፍ እንደሚሆን ለመገመት አያስቸግርም።
በአለማችን ላይ ትልቁን ስፍራ ይዞ ያለው ገንዘብ መሆኑ ግልጽ ነው። እነዚህ አካላት በሚፈጽሙት አስነዋሪ ተግባር ከበስተጀርባው
ገቢያቸውን የሚያዳብሩ ብዙዎች እንደሆኑ ይገመታል። ስለሆነም ከበስተጀርባ ያለው ነገር ካልተስተካከለ እነዚህ አውሬዎች ይጠፋሉ ለማለት
ይቸግራል። የሚገድሉበት መሳሪያው፣ የሚገናኙበት መገናኛው ፣ የሚንቀሳቀሱበት መኪናው , , , ወዘተ በእርዳታ እና በእጅ አዙር
የሚያገኙት ነው። ስለዚህ ዓለማችን ስጋት ውስጥ የወደቀችው በአውሬዎቹ ብቻ ሳይሆን ከበስተጀርባ ሆነው ሰዎችን ከሰውነት ወደ አውሬነት
በማሸጋገር ሚና በሚጫወቱ አካላትም ጭምር ነው።
መቸም የሰው ልጅ ሁሉን ነገር ትምህርት ቤት ገብቶ አይማርም። ክፉንና ደጉን ለይቶ እሚያውቅ፣ የሚያስብና የሚያስታውስ
አእምሮ የተሰጠው በመሆኑ ከአውሬዎች እራሱን መጠበቅ አለበት። በዱር በገደል የሚኖር አውሬ ካለበት ድረስ ከሄዱለት ያለርህራሄ ገድሎ
እንደሚበላ ማወቅ ያስፈልጋል። ምንጊዜም ቢሆን አውሬ አውሬ ነው።
አንዳንዶች በየዋህነት ሲናገሩ እንደምንሰማው እነዚህ አውሬዎች የተነሱበት ኦላማ ከእስልምና ውጭ እንደሆነ ይናገራሉ።
አንዳንድ ሙስሊሞችም እስልምናን አይወክሉም ሲሉ ይደመጣሉ። አብዛኛው ግን ይኸን አይልም። እንደውም የእስልምና ጠበቃ እንደሆኑ አድርጎ
የሚናገር አለ። ምንም ተባለ ምን እነዚህ አውሬዎች እስልምናን የተቀበለ እንደማይገድሉ እያየን ነው። ዓላማቸውም ሁሉን እስላም
ማድረግ ነው። ታዲያ እንዴት እስላም አይደሉም፣ እስልምናን አይወክሉም ልንል እንችላለን? ከሆነስ ለምን የእስልምና ምሁራን በፊትለፊት
ወጥተው አይቃወሟቸውም? ስለዚህ ሃሳቡን ለመቀበል ያስቸግራል። እርግጥ ነው በአሁኑ ወቅት እየሞተ ያለው ክርስቲያን ብቻ አይደለም።
ነገር ግን ዓላማው እስላሞችን ለመግደል ተብሎ ሳይሆን የዓለምን ህዝብ እስላም እናደርጋለን በሚል ጠባብ አስተሳሰብ ነው። ስለዚህ ይህን አውቀን እንደዚህ ዓይነቱን ሃሳብ በአግባቡ ልናስተናግደው
ይገባል።
ሁልጊዜም ቢሆን ለሰው የማይቻለው ለእግዚአብሔር ሁሉ ይቻላልና የአውሬዎቹን ልቦና ወደ ሰውነት እንዲመልስልን ፈቃዱ ይሁንልን።
No comments:
Post a Comment