ይህን ጽሁፍ ከጻፍኩት ሰንበት ብሏል። ምናልባት የእኔ እይታ ሚዛናዊነት
ይጎድለው ይሆን? የሚል ሃሳብ ብልቤ ይመላለስ ስለነበር ከብዙ ሰዎች ሃሳብ ለመውሰድ ሞክሬያለሁ ይሁን እንጅ ተመሳሳይ ስሜቶች ለማየት
ስለቻልኩ ምናልባት ለሚመለከተውን አካል ጥቆማ መስጠቱ ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝን ይሆናል በሚል ሃሳቤን ለመግለጽ ሞክሬያለሁ።
ከወር በፊት በተለያዩ ሚዲያዎች ይንጸባረቅ የነበረው ሃሳብ የብዙዎችን
ቀልብ የሳበ ነበር። አህያውን ፈርቶ ዳውላውን እንዲሉ በቡድን በተደራጀ መልኩ የሰው ህይዎትና ንብረት ሲያጠፉ የነበሩ ወገኖች ሊሰጣቸው ይገባ የነበረውን የስነ ባህርይ ትምህርት
ስለ ሀገር ሰላምና አንድነት ዘብ የቆሙ የአዲስ አበባ ወጣቶችን መንግስት ሰብስቦ በማሰር ስልጠና እየሰጠሁ ነው የሚል መግለጫ ሲሰጥ
ስንሰማ ይህ ነገር ከበስተጀርባው የምንፈውራ ችግር ይኖር ይሆንን? ለማለት ተገደናል? አንድ ጤነኛ የሆነ ሰውን ለህመምተኛ የሚታዘዝ
መድኃኒት ቢሰጡት ከጥቅሙ ጉዳቱ የከፋ ነው። መድኃኒት የሚያስፈልገው ለበሽተኛ ነው። ለጤነኛው ቢሰጡት በውስጡ በሽታውን ካላገኘ ሌላ የስሜት ህዋሱን ይጎዳና
ለሌላ ችግር ይዳርገዋል።