Friday, April 6, 2018

በትንሳኤ ላይ ትንሳኤ

ክርስቶስ አንድ ጊዜ ሞቶ የሰውን ልጆች ነጻ ካወጣ በኋላ በክብር ተነስቷል። በዚህም ምክንያት በእርሱ ያመኑ ክርስቲያኖች የትንሳኤውን እለት በየዓመቱ ያከብሩታል። ሞቱን ስናስብ ሞተን እንደነበር እናስባለን ትንሳኤውን ስናከብር ሞተን እንደማንቀር በክብር እንደምንነሳ እንናገራለን። ስለዚህ በእርሱ ያመኑ ሁሉ ሞቱንና ትንሳኤውን ያስቡ ዘንድ ይገባል።

የክርስቶስን ትንሳኤ ከውድቀት ከመነሳት ጋር ብናከብረው እውነተኛ ትንሳኤ ይሆናል። እኛ ሳንነሳ እሱ ተነሳ ብንል ትርጉሙ አልገባንም ማለት ነው። ከክፋት፣ከተንኮል፣ ከምቀንነት፣ ከዘረንነት ወንበር ላይ ተነስተን የፍቅርና የሰላም ዓርማ የሆነውን መስቀሉን ይዘን የክፋት ሁሉ ባለቤት የሆነውን ሰይጣን ዲያቢሎስን ከእግራችን በታች መጣል ካልቻልን የክርስቶስ ትንሳኤ ተካፋዮች እንዴት ልንሆን እንችላለን? ስለዚህ በየደረጃው ያለን ሁላችን አንዱ ጌታ ስለሁላችን ሞቶ ትንሳኤን እንዳጎናጸፈን ከያለንበት የክፋት ባርነት መንፈስ ተላቀን ለመነሳት የሰላምና የፍቅርን ጋሻ ጦር እንልበስ።


የ2010 ዓ/ም የሁዳዴን ጾም ስንጀምር ስለ ውድቀት እያወራን ተስፋ በጠፋበት ማእበል ውስጥ ሆነን ነበር። ወደ ፋሲካው ስንቃረብ የጠፋው ተፋችን እየለመለመ አየነው። ኢየሀድጋ ለሀገር ዘእንበለ አሃዱ ሔር ( ሀገርን ያለ ጠባቂ አይተዋትም) እንደተባለው ለሀገሪቱ የሚበጁ ሁኔታዎች በመታየታቸው ትንሳኤን ልናይ የምንችልበትን ተስፋ እንድንሰንቅ አድርጎናል።

ለኢትዮጵያ ሰላምና እድገት የሚመኙ ኢትዮጵያውያን ብቻ አይደሉም። የዓለምን ታሪክ የሚያውቁ ኢትዮጵያ ለዓለም ያበረከተችውን አስተዋጽኦ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ በየ እለቱ አዳዲስ መረጃዎችን ለዓለም ህዝብ ያቀርባሉ። እኛ ልጆቿ በተለያየ ጎራ ተሰልፈን ውድቀቷን ስናፋጥን ልጆቿ ያልሆኑ ነገር ግን ታሪኳን የሚያውቁ በዓለም መድረክ ይተርኳታል። 

የሰይጣን አይኑም ጆሮውም ይደፈንና ኢትዮጵያ በጌታ ትንሳኤ የሰላምና የእርቅ መንፈስ ግባ የጸብና የመለያየት መንፈስ ውጣ የሚባልባት ሀገር ,  , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , ,?  እንቀጥላለን 




No comments:

Post a Comment