Monday, January 23, 2012

ይሉኝታ

በተነሳሁበት ርዕስ ዙሪያ ብዙ ጸሐፍያን እንደጻፉ፣ ወደፊትም እንደሚጽፉ እገምታለሁ። ነገር ግን ዛሬ ባለንበት ዘመን « ይሉኝታ » በብዙ ሰዎች ዘንድ የተዘነጋ በመሆኑ፣ አስፈላጊነቱንና አልፎ አልፎ ግን አላስፈላጊ የሚሆንበትም አጋጣሚ እንዳለ ለመጠቆም ያህል ነው። በተለይ ደግሞ በካህናት ዘንድ ከአስነዋሪ ተግባራት በስተቀር በይሉኝታ የምናልፋቸው ነገሮች ሊኖሩ እንደማይገባ በቅዱስ ወንጌሉ ተምረናል።ወንጌልንም ባልሰብክ ወዮልኝ 1ኛቆሮ 9፥16  ወንጌል ማለት ደግሞ እውነት ነው እንደጊዜው ሁኔታ እየተለዋወጡ የሚኖርበት አይደለም። ነገር ግን እግዚአብሔርን የማያስደስት ነገር ስንሰራ ሰውንም ሆነ እግዚአብሔርን ምን ይለኛል ማለት ይገባናል።

Saturday, January 21, 2012

ከእኔም ተማሩ

በቤተክርስቲያናችን በየዓመቱ ጥር 11 ቀን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጥምቀት ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ በታላቅ ድምቀት ይከበራል። በዓይነቱ ልዩ የሆነ በዓልም እናደርጋለን። ይህ ለምን ሆነ ብንል፣ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ የፈጸማቸው ነገሮች በሙሉ በቤተክርስቲያናችን ትርጉም ስላላቸው ነው። ሌሎችአብያተ ክርስቲያናት የጌታን በዮርዳኖስ በዮሐንስ እጅ መጠመቅ ከመናገር ያለፈ ትርጉም አይሰጡትም።

Wednesday, January 4, 2012

« መድኃኒነ ተወልደ ነዋ »

                                                 
                                     «  መድኃኒታችን እነሆ ተወለደ »
                             ቀሲስ ዘለዓለም ጽጌ  kesiszelealem@Gmail.com
የሰው ልጅ ለአምስት ሽ አምስት መቶ ዘመን በኃጢአት ደዌ በጸና ታሞ የሚፈውሰው መድኃኒት በማጣቱ በጨካኙ በዲያቢሎስ አገዛዝ ስር ወድቆ የፍዳና የኩነኔ ዓመታትን አሳልፏል። ተቆራኝቶት የነበረው ሰው ሊፈውሰው የማይችለው ደዌ ስለነበረ  በየዘመኑ የተነሱ ጠቢባን ብዙ ቢደክሙም መድኃኒት ማግኘት ግን አልቻሉም ነበር።
ቢሆንም ግን የተያዘበት በሽታ ባለመድኃኒቱ እስኪገለጥ ድረስ ቢያሰቃየውም  ፈጽሞ እንዲያጠፋው የፈጣሪው ፈቃድ አልነበረምና ያንን መድኃኒት በየዘመኑ የነበሩት አበው ተስፋ ባለመቁረጥ ሲጠብቁ ኖረዋል። « እግዚአብሔር ሆይ፥ መድኃኒትህን እጠብቃለሁ። ዘፍ 49፥18

Sunday, January 1, 2012

መንጋውን ለሚተው ለምናምንቴ እረኛ ወዮለት! ት,ዘካ 11፥17

ዛሬ እለቱ ታህሳስ 22/ 2004 ዓ/ም ሲሆን  እንደ ቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ በዚህ እለት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የመጽነሷን ዜና የነገረበት እለት ነው። ከዚሁም ጋር እለቱ እለተሰንበት ላይ ስለዋለ ድርብ በዓል ነው። ታላቁ የቤተክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ ያሬድ የዛሬውን ሰንበት ኖላዊ ወይንም ደግሞ መልካም እረኛ የሚል ስም ሰጥቶታል። ያለፉት ሁለት ሳምንታት እና የዛሬው ሰንበት የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ከድንግል ማርኃም በስጋ መወለድ እያሰብን የልደቱን ብርሃን ለማየት በተስፋ ደጅ የምንጠናበት ነው።