የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ቤተክርስቲያን ከሌሎች ልዩ የሚያደርጋት በጎ ሥራዎችንና መልካም ያደረጉ ሰዎችን አክብራ ለትውልድ እንዲተላለፍ ማድረጓ ነው። መቼም
በጎ ነገር ሲታወስ ክፋቱም አይረሳምና ለትምህርት እንዲሆን ይዘከራል። ስለ ቃየን ባንሰማ ኖሮ የአቤልን ደግነት ልንረዳው አንችልም
ነበርና።
የነነዌ ሰዎችን ስናስብ
የእግዚአብሔርን ቸርነትና ከሃሊነት፣ የዮናስን አለመታዘዝ፣ የኃጢአታቸውን መጠን፣ እንዲሁም ለንስሃ ታዛዥነታቸውን እናገኛለን።
እግዚአብሔር
ቸርና መኃሪ አምላክ መሆኑን ከቅዱሳት መጻህፍት ተረድተን በህይዎታችን አውቀነዋል። እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ ‘’እርሱ ግን መሓሪ
ነው፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር
አላቸው፥ አላጠፋቸውምም፤ ቍጣውንም
መመለስ አበዛ፥ መዓቱንም
ሁሉ አላቃጠለም’’ መዝ 78፥38 እዚህ ላይ ልንገነዘበው የሚገባው የእግዚአብሔር
ቸርነት ወደ ንስሃ የሚያቀርብ እንጅ የሰውን ልጅ ነጻነት የሚከለክል እንዳልሆነ ማስተዋል ያስፈልጋል።
|
ነቢዩ ዮናስ የእግዚአብሔርን
ትእዛዝ አልቀበልም ያለው እግዚአብሔር ቸርና መኃሪ አምላክ መሆኑን ያውቃል እንዲሁም የነነዌ ሰዎች ኃጢአት ብዙ መሆኑን ተረድቷል
ትጠፋላችሁ ብየ ተናግሬ በይቅርባይነቱ ቢምራቸው ሃሰተኛ ነቢይ እባላለሁ ብሎ እንደሆነ እንረዳለን ይሁን እንጅ ከእግዚአብሔር ማምለጥ
እንማይቻል ከዮናስ ህይዎት በብዙ እንማራለን።
በኃጢአት ላይ ስልጣን የተሰጣት
ንስሃ ያላትን አቅምና ጉልበት ከነነዌ ሰዎች ታሪክ መማር ይቻላል። ከዚሁ ጋር እነዚህ ግዝቦች ንስሃቸው ተቀባይነት ያገኘው የበደሉት
በአንድነት በመሆኑ ንስሃም የገቡት በአንድነት ነበር ‘’የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን
አመኑ፤ ለጾም አዋጅ
ነገሩ፥ ከታላቁም ጀምሮ
እስከ ታናሹ ድረስ
ማቅ ለበሱ።ወሬውም
ወደ ነነዌ
ንጉሥ ደረሰ፤ እርሱም
ከዙፋኑ ተነሥቶ መጐናጸፊያውን
አወለቀ ማቅም ለበሰ፥
በአመድም ላይ ተቀመጠ። አዋጅም
አስነገረ፥ በነነዌም ውስጥ
የንጉሡንና የመኳንንቱን ትእዛዝ
አሳወጀ፥ እንዲህም አለ፦
ሰዎችና እንስሶች ላሞችና
በጎች አንዳችን አይቅመሱ፤
አይሰማሩም ውኃንም አይጠጡ፤ሰዎችና
እንስሶችም በማቅ ይከደኑ፥
ወደ እግዚአብሔርም
በብርቱ ይጩኹ፤ ሰዎችም
ሁሉ ከክፉ
መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው
ግፍ ይመለሱ።እኛ
እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ
ይጸጸት እንደ ሆነ፥
ከጽኑ ቍጣውም ይመለስ
እንደ ሆነ ማን
ያውቃል?እግዚአብሔርም ከክፉ
መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን
አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው
ዘንድ በተናገረው ክፉ
ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም’’ ዮና 3፥5
የነነዌ ሰዎች የእምነት
ጥንካሬ የተገለጸው አስቀድሞ በደላቸው ጎልቶ የወጣ በመሆኑ እንደሆነ
እንረዳለን። ለብርሃን ውበት የጨለማን አስተዋጽኦ የሚያውቀው ብልህ ብቻ ነው። የነነዌ ሰዎች አስተማሪ በማጣት ኃጢአትን
ተለማምደው እግዚአብሔርን እንዳሳዘኑት ታሪካቸው ይነግረናል። እግዚአብሔርም ሊያስተምራቸው እንጅ ሊያጠፋቸው አልወደደም። በዚህም
ምክንያት ዮናስን ልኮ ከስህተታቸው እንዲመለሱና ንስሃ እንዲገቡ ነግሯቸዋል። የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው በመጸጸታቸው የብዙ ዘመን
ኃጢአታቸው በሦስት ቀን ጾምና ጸሎት ተወግዶላቸዋል።
በቅዱስ መጽሐፍ እንደምናነበው
በተለያዩ ዘመናት የተለያዩ ህዝቦች እውነተኛውን መንገድ የሚያሳያቸው በማጣት በስህተት ጎዳና ተጉዘው በኃጢአታቸው ምክንያት ጠፍተዋል።
የሰው ልጆች የኃጢአት ጥግ ላይ በመድረሳቸው ኤልሻዳይ የሆነው አምላክ ሰውን በመፍጠሩ እንደተጸጸተ በቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ ተብሎ
ተጽፏል ”እግዚአብሔርም ሰውን
በምድር ላይ በመፍጠሩ
ተጸጸተ፥ በልቡም አዘነ” ዘፍ 6፥6 ምንም እንኳን እንደዛሬው
ምድሪቱ በሰዎች ባትጨናነቅም በዚያ ዘመን ካሉ ህዝቦች መካከል አንድ ኖህ ብቻ ነበር እውነተኛ ሆኖ የተገኘው በመሆኑም
ከኃጢአታቸው እንዲመለሱ ነግሯቸው ነበር እውነትን ለመናገር ብቻውን
በመሆኑ የሚሰማው አላገኘም።
ሰውን ከኃጢአት ዓለም ከማውጣት
ይልቅ ቀላሉ ሥራ ወደ ኃጢአት እንዳይሄድ ማድረግ ነው። ተጣሞ ያደገን ዛፍ አቃናለሁ ቢሉ ውጤቱ መሰበር ነው። ልጆችን ከህጻንነት
ጀምሮ በስነምግባር አንጾ ማሳደግ የሚያስገኘውን ጥቅም ቤተክርስቲያናችን ሁልጊዜ የምትነግረን ከዚህ የተነሳ ነው።
በቤተክርስቲያናችን ሥርዓት
በየዓመቱ የነነዌን ሰዎች እንድናስባቸው አባቶቻችን ሥርዓት የሰሩልን በኃጢአት ዓለም ብንኖርም እንኳን ወደ ንስሃ የሚመለስ ልብ ካለን እግዚአብሔር
ቅርብ መሆኑን አውቀን ተረድተን ወደ ንስሃ እንድንመለስ ነው።
ኃጢአትን ተለማምዶ ኖሮ
ወደ ንስሃ መመለስ ከባዱ ፈተና ነው። የነነዌ ሰዎች በደላቸው ተዘርዝሮ ባይጻፍም ክፋታቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደደረሰ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል ’’ የእግዚአብሔርም
ቃል ወደ
አማቴ ልጅ ወደ
ዮናስ እንዲህ ሲል
መጣ ተነሥተህ ወደዚያች ወደ
ታላቂቱ ከተማ ወደ
ነነዌ ሂድ፥ ክፉታቸውም
ወደ ፊቴ
ወጥቶአልና በእርስዋ ላይ
ስበክ’’ ዮና,
1፥1
No comments:
Post a Comment