የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ቤተክርስቲያን ከሌሎች ልዩ የሚያደርጋት በጎ ሥራዎችንና መልካም ያደረጉ ሰዎችን አክብራ ለትውልድ እንዲተላለፍ ማድረጓ ነው። መቼም
በጎ ነገር ሲታወስ ክፋቱም አይረሳምና ለትምህርት እንዲሆን ይዘከራል። ስለ ቃየን ባንሰማ ኖሮ የአቤልን ደግነት ልንረዳው አንችልም
ነበርና።
የነነዌ ሰዎችን ስናስብ
የእግዚአብሔርን ቸርነትና ከሃሊነት፣ የዮናስን አለመታዘዝ፣ የኃጢአታቸውን መጠን፣ እንዲሁም ለንስሃ ታዛዥነታቸውን እናገኛለን።
እግዚአብሔር
ቸርና መኃሪ አምላክ መሆኑን ከቅዱሳት መጻህፍት ተረድተን በህይዎታችን አውቀነዋል። እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ ‘’እርሱ ግን መሓሪ
ነው፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር
አላቸው፥ አላጠፋቸውምም፤ ቍጣውንም
መመለስ አበዛ፥ መዓቱንም
ሁሉ አላቃጠለም’’ መዝ 78፥38 እዚህ ላይ ልንገነዘበው የሚገባው የእግዚአብሔር
ቸርነት ወደ ንስሃ የሚያቀርብ እንጅ የሰውን ልጅ ነጻነት የሚከለክል እንዳልሆነ ማስተዋል ያስፈልጋል።
|