በአንድ ወቅት አንድ መልካም ሰው ወንጀል ሰርተሃል ተብሎ ፍርድ ቤት ቀረበ አሉ፤ ታዲያ ይህ ሰው ወንጀሉን የፈጸመው ሆን ብሎ ሳይሆን።በአጋጣሚ ነበር፥ ፍርድ ቤት ቀርቦ ዳኛው የምስክሮች ቃል ከሰሙና የቀረበላቸውን ማስረጃ ከመረመሩ በኋላ በሞት እንዲቀጣ ወሰኑበት። በዚህ ጊዜ በፊቱ ላይ ምንም የመረበሽ ስሜት አልታየበትም ነበር። በሁኔታው የተገረሙት ዳኛውና በዙሪያው ያሉት ሰዎች የመጨረሻ የመሰናበቻ ቃሉን ይጠብቁ ጀመር። እግዚአብሔር ይስጥልኝ ክቡር ዳኛ፣ እድሜ ይስጥልኝ፣ ፍርድ የሚሰጥ ዳኛ አያሳጣን ወ ዘ ተ እያለ ምስጋናውን ያወርደው ጀመር አግራሞታቸው የጨመረው ዳኛ ግራ ተጋብተው ,, የፍርዱን ውሳኔ የተረዳው አይመስለኝም በሞት እንዲቀጣ ነው የተወሰነበት ምናልባት ውሳኔውን በደንብ ካልሰማ አስረዱት,, አሉ ። ሰውየውም መለሰ ,, ውሳኔውን በደንብ ተረድቻለሁ ፍርዱም ገብቶኛል የመረዳትም ችግር የለብኝም,, ብሎ መለሰ፤ የዳኛው ጥያቄ ቀጠለ ,, ታዲያ እንዴት ነው የሞት ፍርድ እየተፈረደብህ ፍርድ ቤቱን የምታመሰግነው? አሉ ። ,, ጌታየ ከዚህም የከፋ ፍርድ እኮ አለ መቶ ጅራፍ ተገርፎ ይሙት ቢሉስ ይችሉ አልነበር? ብሎ መለሰ ይባላል።
መቸም በምድር ላይ ስንኖር ስህተት የምንሰራበት መንገዱ ብዙ ነው። አይጣል አያድርስ እንጅ ከክፉ ሰው ጋር ከዋልን ክፉ ስራውን ወደኛ ሊያስተላልፍብን ይችላል። በሰው ክፉ ሃሳብ ተመርተው ያልሆነ ስህተት የሚሰሩ ሰዎች በየጊዜው ይታያሉ። አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው። በዓለም ላይ ወንጀለኛ ተብለው የሚፈረድባቸው ሁሉ ወንጀልን ሆን ብለው ሰርተውት ሳይሆን በዓለም ውስጥ ያለው ክፉ ወጥመድ ጠልፎ የጣላቸው ናቸው። ነገር ግን ሆን ብለው ወንጀልን ለመስራት ሌት ተቀን እንቅልፍ አጥተው ጉድጓድ ሲምሱ የሚኖሩ ብዙ ሰዎች በሰላም ይኖራሉ። ይህ የዓለም ጸባይ ነው። ዓለም የማይመቻት በሆነው ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን ማለት ነው።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልዕክቱ ,, ማንም ለሌላው በክፉ ፈንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፥ ነገር ግን ሁልጊዜ እርስ በርሳችሁ ለሁሉም መልካሙን ለማድረግ ትጉ። ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና,, 1ኛ ተሰ 5፥15 ብሎ እንደተናገረው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚያ በመከራ ሰዓት የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው እያለ የሚሰቅሉትን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበር።

የዘመኑ ትውልድ የስልጣኔው መጀመሪያ የሚያደርገው ተመስገን አለማለትን ነው። የቀድሞዎቹ አባቶቻችን እናቶቻችን ክፉ ተደርጎባቸውም አንኳ እግዚአብሔር ይስጥልኝ እና እግዚአብሔር ይመስገን ማለት ባህላቸው ነበር። በጎ ውለታን አስቦ ስህተት እንኳን ቢኖር ይቅር የሚል ልቦና ነበራቸው። የመጨረሻው ዘመን ላይ የመድረሳችን ምልክቶች ጎልተው እየታዩ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለመንፈስ ቅዱስ ልጁ ለጢሞቴዎስ በጻፈለት በሁለተኛው መልእክቱ ስለመጨረሻው ሰዓት እንዲህ ብሎት ነበር ,, ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥
የማያመሰግኑ ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤ የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።2ኛ ጢሞ 3፥2
ሃገራችን ኢትዮጵያ ከምትታወቅባቸው በጎ ስራዎች አንዱ ታሪክን ጠብቃ ሳይበረዝ ሳይከለስ ለትውልድ ማስተላለፏ ነው። ዛሬ ላይ አንዳንድ በጎ ህሊና የጎደላቸው ግለሰቦች ይህን የሚቃረን ተግባር እየፈጸሙ ይገኛሉ። እንኳን ለዓለም ድንቅ ውለታ የዋሉ ቅዱሳንን ይቅርና ምንም በጎ ስራ ባይሰሩ በየዘመኑ እግዚአብሔር ያስነሳቸውን ሰዎች ታሪክ ጽፋ ለትውልድ ማስተማሪያ በክብር ታስቀምጠዋለች።
ሃይማኖት ያለው ሰው ,, ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም,, ዮሐ 1፥3 ብሎ ያምናል። ስለዚህ በየዘመኑ የተሰሩ በጎ ስራዎችን ለትውልድ ማስተማሪያነት መጠቀም፥ የታሪኩን ባለቤት ማክበርና ማመስገን ከሰው ልጆች የሚጠበቅ ነው።
አሁን ለምናያቸው አንዳንድ ችግሮች ምክንያቱ ትውልዱ ልዩ ልዩ እንግዳ ትምህርትን እየተከተለ ከእውነተኛው ሃይማኖት እራሱን እያገለለ በመምጣቱ ነው። የዛሬን አያድርገውና አህዛብ በምድራቸው በነጻነት መኖር ስላልቻሉ በመሪያቸው አማካኝነት በጎና ቅን ለሰዎች የሚራራ የሃበሻ ንጉስ ዘንድ ሂዱ በዚያች ሃገር እንግዶች ይከበራሉ፣ ድሆች መጠጊያ ያገኛሉ ተብለው ወደ ሃገራችን እንደመጡ ታሪክ ይነግረናል። እንደተባለውም ወደ ሃገራችን መጥተው የጥገኝነት ጥያቄ በማቅረባቸው በዘመኑ የነበረው ንጉስና ህዝቡ እግዚአብሔርን የሚያመልኩ፣ እንግዳ ተቀባዮች ስለነበሩ በፍቅር ተቀብለው አስተናግደዋቸዋል። የአህዛብን እምነት ይዛችሁ ስለመጣችሁ አንቀበልም አልተባሉም። ይልቁንም መጠጊያ ተሰጥቷቸው ከነእምነታቸው በሰላም እንዲኖሩ ተደርገዋል። ይህ ለሁልጊዜ ሊረሳ የማይገባ ውለታ ነው። የሰው ልጅ አንዳንድ ጊዜ በጎ ሥራ ለመስራት እውቀት ላይኖረው ይችላል፥ ሰዎች ሲሰሩ አይቶ አለመስራት ግን በጎ ህሊና ማጣት ነው። በሃገራችን ያሉ ሙስሊሞች ይህኸንን ሊዘነጉ አይገባም ። እኛ ብቻ ነን መኖር ያለብን፣ ክርስትና መጥፋት አለበት የሚሉ መምህራኖቻቸውም ወደ ህሊናቸው መለስ እንዲሉና ታሪክ እንዲመረምሩ እናሳስባለን።

ሰው በሃይማኖት መኖር ካልቻለ ታሪክ ያዛባል፥ ያለፈውን ከመጠበቅ ይልቅ ማጥፋት ይቀናዋል። ስለዚህ በሃይማኖት ኖሮ እራሱን መመርመር ይገባዋል። ኢትዮጵያውያን እያጣነው የመጣነው ነገር በጎ የሰሩ ሰዎችን ታሪክ ማክበርና አርዓያነታቸውን ተከትሎ ለትውልድ የሚተርፍ በጎ ሥራ መስራትን ነው።
ከሃይማኖታቸው ፈቀቅ ያሉ፣ በአህዛብና በመናፍቃን የተማረኩ ወገኖች እውነተኛዋን ቤተክርስቲያን ሲነቅፉና ሲሳደቡ ይሰማሉ። ቤተክርስቲያን ግን እንኳን መነቀፍ ብዙ ውለታ ሊከፈላት በተገባ ነበር። ለዓለም ድህነት ውለታ የዋለች የአምላክን እናት ቅድስት ድንግል ማርያምን፣ ቅዱሳንን አክብራ ማስከበሯ ለዲያቢሎስና ለሰራዊቱ አልተመቸውም። ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ ሃይማኖታችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን አክብራና አግና ስሟን የምትጠራው እኮ ለዓለም ውለታ ስለዋለች ነው። የሰው ዘር በሙሉ በጽድቅ ራሃብና ጥም በሚሰቃይበት ዘመን እውነተኛ የህይወት ምግብንና የህይወት መጠጥን የሰጠች እናት እኮ ስለሆነች ነው፥ ዘመን አመጣሽ መናፍቃን ይህን አይቀበሉም። እንኳን እናቱን ይቅርና የሱንም ስም በከንቱ ሲጠሩት እንሰማቸዋለን። ስድብ የዲያቢሎስ እንደሆነ ከትውልዱ ማን አስተዋለ? ,, ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው,, ራዕ 13፥5 ስለ ዓለም ሰላም ስለ ፍጥረት ፍቅርና አንድነት ሲጸልዩና ሲያማልዱ ህይወታቸውን ያሳለፉ ቅዱሳንን የሚነቅፍ ትውልድ ላይ መድረሳችን ያሳዝናል። ሃገርን ከጠላት ህዝብን ከችግር ለማዳን የደከሙ ነገስታት መከበር ሲገባቸው ምስጋና የማያውቅ ትውልድ በመቃብራቸው ላይ ቆሞ በጎውን ስማቸውን ለማጉደፍ ተነስቷል። ይህ የሚያሳየው ያለንበት ዘመን የጥፋት እንጅ የልማት አለመሆኑን ነው። ,,ዮሴፍን የማያውቅ ንጉስ ተነሳ,, ዘጸ 1፥8 ተብሎ እንደተጻፈውi ያባቶቹን ታሪክ የሚያጎድፍ ውለታቸውን የማያውቅ ፥በጎ ሥራ ሰርተው ያስቀመጡለትን ታሪክ ጥላሸት የሚቀባ ትውልድ ሃገራችን እያበቀለች ነው።
የታሪክ አደራ ያለባቸው አባቶች ይህን ለትውልዱ ማስተማር ይጠበቅባቸዋል። ዝምታ በጉዳዩ እንደመስማማት ያስቆጥራልና ትውልዱ ታሪክ ሰሪ እንጅ ክፉ ሰዎች የሚዘሩትን የሃሰት ምስክርነት እየሰማ የሚጠበቅበትን ከመስራት እንዳይዘናጋ መንገር ያስፈልጋል። አንዳንዶች የፖለቲካ ፍጆታ ለማግኘት፥ አንዳንዶች ታሪክ ባለማወቅ ዘመኑ የፈጠረውን መገናኛ በመጠቀም እንክርዳድ እየዘሩ ይገኛሉ፥ መልስ የሚሰጣቸው ካልተገኘ ይህ የክፋት መርዛቸው ይሰፋና በአንድነቷና በሉአላዊነቷ ተከብራ ለኖረችው ሃገራችን የማይመች ገጽታን ይፈጥራል። ,, የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው ,, ዕብ 13፥7 እንደተባለው ባባቶቹ እግር ተተክቶ ታሪክ የሚሰራ ትውልድ፥ ማፍራት ባለመቻላችን በእምነቱ አባቶቹን የሚመስል፣ በኑሮው መልካም ፍሬን የሚያፈራ አልሆነም፥ ይልቁንም እግዚአብሔር በሰጣቸው ዘመን ክፉም ሆነ በጎ ሰርተው አረፍተ ዘመን ገድቧቸው በሞት የተወሰዱ አባቶቹን የሚወቅስ ሆኗል። ከሰው ስህተት ከብረት ዝገት እንዲሉ አባቶቻችን፥ ሰውን ፍጹም መሆን አለበት ብሎ ማሰብ አላዋቂነት ነው።
ያሁኑ ትውልድ ወቃሽ እንጅ አመስጋኝ አይደለም። መራገም እንጅ መመረቅ አይቀናውም። የቀድሞዎቹ ግን ባለፈው ዘመን በነበሩ አባቶቻቸው የሚምሉ፥ በአባቶቻቸው ስም በጎ ነገር ከፈጣሪያቸው የሚለምኑ ነበሩ፥ ነቢየ እግዚአብሔር ኤልያስ እግዚአብሔር የመረጠው፥ በዘመኑ ብዙ ድንቅ ስራወችን የሰራ ሰው ነበር። የኤልዛቤልን የጣኦት ካህናት ባሳፈረበት ጸሎቱ እንዲህ ነው ያለው፥ ,, አቤቱ፥ የአብርሃምና የይስሐቅ የእስራኤልም አምላክ ሆይ፥ አንተ በእስራኤል ላይ አምላክ እንደ ሆንህ፥ እኔም ባሪያህ እንደ ሆንሁ፥ ይህንም ሁሉ በቃልህ እንዳደረግሁ ዛሬ ይገለጥ 1ኛ ነገ 18፥36 ነቢዩ ቅሩበ እግዚአብሔር የነበረ ነው። ነገር ግን ከሱ በፊት የነበሩትን አባቶቹን እያከበረ ነው ወደ ፈጣሪው ይጸልይ የነበረው።
ስለዚህ ትውልዱ ያለፈውን ስህተት እየቀፈረ በጎ ስራ ሊሰራበት የሚገባውን ዘመን በከንቱ ማቃጠል የለበትም። ቀድሞ የነበሩ አባቶቻችን እናቶቻችን በመሃል ጣልቃ እየገባ ሃገራቸውን ለማጥፋት ይሰማራ የነበረውን የውስጥም ሆነ የውጭ ጠላት ነቅተው ተግተው በመጠበቃቸው ነው ዛሬ ላይ በሃይማኖቷና በባህሏ የምታኮራ ሃገር እንድትኖረን ያደረጉት። ይህን የሚዘነጋ ካለ እውነትም ኢትዮጵያዊ መሆኑ ያጠራጥራል።

No comments:
Post a Comment