የዘመናትን መለዋወጥ ስናነሳ ባለጊዜዎችን ማውሳታችን አይቀሬ ነው። እስቲ ሁላችንም አንድ ነግር እራሳችንን እንጠይቅ, ዘመን የሚሄደው ወደ ፊት ነው ወደ ኋላ? መልሱ ሊሆን የሚችለው ወደ ፊት ነው። የሚገርመው ነገር ግን ዘመን ወደ ፊት ሲሄድ ባለ ዘመኖች ወደ ኋላ መሄዳቸው ነው።
Tuesday, December 31, 2013
Friday, December 27, 2013
ከሰው ስለቆጠርከኝ አመሰግንሃለሁ
አንድ ጊዜ የጣለው ሰው በአንድ ሃገር ይኖር ነበር ይባላል። ይህ ሰው ቀድሞ ብዙ ሃብትና ንብረት የነበረው ፣ በሰዎች ዘንድ የተከበረ፣ ባለው ሃብትና ንብረት የተነሳ ብዙዎች የሚወዱት ሰው ነበር። የዚህ ዓለም ሃብት ሲመጣም ድንገት ሲሄድም ድንገት ነውና ሰውየውም ብልሃትና ጥበብ የጎደለው ሰው ስለነበር ሃብቱ እያለቀ መጣ። በዚያው ልክ የወዳጆቹም ፍቅር እየቀዘቀዘ መሄድ ጀመረ። ዓለም ቁልቁለት ላይ ካገኘችን ርህራሄ የላትምና ባጭር ጊዜ ውስጥ ያለው ሃብቱ ሁሉ አለቀ። በቤቱ ውስጥ የነበረውን ንብረት በሙሉ እያወጣ ሸጦ ጨረሰው። በጎረቤቶቹ ዘንድ ቀድሞ የነበረው ታሪክ ተቀይሮ የተጠላና የተናቀ ሆነ። ከሃብቱ ከንብረቱ ይልቅ በሰው ዘንድ መናቁ እጅጉን አሳዘነው። ቀድሞ ከቤቱ ሲወጣ ከበሩ ላይ ተኮልኩለው ከእጁ ምጽዋት የሚጠባበቁ ነዳያን ሳይቀር ይዘባበቱበት ጀመር።
Subscribe to:
Posts (Atom)