አባቶቻችን ስለ ነገሩን ብቻ ሳይሆን ሀገር በተግባሯ እናትን ትመስላለች። የተፈጥሮን ህግ ጥለን እንደ እንስሳት እንሁን ካላልን በቀር የአንድ እናት ልጆች ወንድማማቾች፣ እህትማማች ይባላሉ። ይህን መቀበል የማይፈልግ ትውልድ የአንድ እናት ልጅ ወይም የአንድ ሀገር ህዝብ ሊባል ከቶ እንዴት ይችላል? ብዙ ጊዜ በጎውን ደጋግመን እያወራን ክፉው ነገር አስተዋይ በማጣቱ ከአቅም በላይ እያደገ የመጣ ይመስላል። ጤናማ ያልሆኑ ሃሳቦችን እውነት ነው እያልን ስንቀበል በመኖራችን ዛሬ ላይ ያለነው ትውልዶች የራሳችንን ስንፍና ወደ ጎን በመተው፤ ህይዎታቸውን ያለ ስስት ለሀገራቸው በመስጠት ሀገር ያስረከቡንን አባቶቻችንን ሽቅብ የምንራገም ተስፋ አልባ፣ ወደ ኋላ እንጅ ወደፊት ማየት የማንችል ትውልዶች ሆነናል።
Where is Ethiopia?














ሰሞኑን በሀገራችን እየሆነ ያለውን ማቆሚያ የሌለው የሚመስል እንስሳዊ ተግባር ሲፈጸም የተመለከተ ሁሉ ለማመን በመቸገር በዘመናችን በ technologie ፈጠራ ከሚሰሩ ትእይንቶች ጋር እያነጻጸረ እውነትነቱን ለመቀበል ሲቸገር ለማየት ችለናል። ለካ ከ10% በርሰንት በላይ በፍጥነት እያደግን ነው ሲባል የነበረው እንዲህ ተገልጦ ስላላየነው እንጅ የራሱ እውነት ነበረው እንዴ? ለካ እንዲህ ዓይነት እድገትም አለ?
እንደኔ ለብዙ ዓመታት በሰው ሀገር ለኖረ ሰው ይህ ዘመን እጅጉን የከፋ ዘመን ነው ማለት ይቻላል። በሰው ሀገር የሚኖር ሰው ከመንግሥተ ሰማያት በላይ የሚናፍቀው ሀገሩን ነው። ይህን ናፍቆት ተሸክሞ እየኖረ የሀገር መርዶ ሲመጣለት የሚሸከምበት አቅም ሊኖረው አይችልም።
እንደኔ ለብዙ ዓመታት በሰው ሀገር ለኖረ ሰው ይህ ዘመን እጅጉን የከፋ ዘመን ነው ማለት ይቻላል። በሰው ሀገር የሚኖር ሰው ከመንግሥተ ሰማያት በላይ የሚናፍቀው ሀገሩን ነው። ይህን ናፍቆት ተሸክሞ እየኖረ የሀገር መርዶ ሲመጣለት የሚሸከምበት አቅም ሊኖረው አይችልም።
ትላንት እንደቀላል ይታዩ የነበሩ ጉዳዮች ዛሬ ላይ ገዝፈው እውነት ያልነበሩ ከእውነት ተቆጥሩው በቀላሉ ተሰቅለው ለማውረድ የሚያስቸግሩ ሆነው እያየናቸው ነው። "በጎመኑ በቀጣኽበ" እንዲሉ ትላንት ችላ ያልነው ነገር ዛሬ ላይ የማይታረቅ ትውልድ አፍርተን ሀገራችን ሰላም አልባ በረት እንድትሆን አድርገናታል።
በግሌ መልስ ያጣሁለት ነገር ግን መልስ የሚያሻው ሃሳብ ላነሳ እወዳለሁ። እኛና እነሱ የሚለው ነገር ጥቅሙ ከምን አንጻር ታይቶ እንደሆነ የሁልጊዜ ጥያቄየ ነው። እኛ አማራዎች፣ እኛ ኦሮሞዎች፣ እኛ ትግሬዎች ወ.ዘ.ተ በሚለው ስም የምንፎክር ከሆነ ኢትዮጵያ የማን ልትሆን ነው? ምንያህልስ ኋላቀር አስተሳሰብ እንደሆነ ተረድተነዋል? እራሳችን ግራ ተጋብተን ዓለምን ግራ እያጋባን እንደሆነ ታውቆን ይሆን? አንድ የወንጌል ሰባኪ "ዓለም የሚያውቀን ኢትዮጵያ በሚለው ስማችን ነው" እንዳሉት እኛ ኢትዮጵያውያን ለማለት እንዳንችል አዚም ያደረገብን ማነው? ሀገሪቱ ለምታ በረሀብ፣ በስደት የሚሰቃዩ ወገኖቻችን ከውርደት ቢላቀቁ ምንድነው ክፋቱ? መቸም እንደዚህ እየተበላላንና እየተነካከስን ሀገር እናለማለን ማለት ሹፈት ነው።
ባለፉት ዓመታት በየጊዜው በሚፈጠረው ችግር ምክንያት የትምህርት መጓደል ይታይ እንደነበር የታወቀ ነው። ወጣቱ በእውቀት አእምሮውን አበልጽጎ ለሀገር እድገትና ብልጽግና አስተዋጽኦ እንዳያደርግ ምን ያህል ተጽእኖ እንደፈጠረበት ከተግባሩ ማየት ይቻላል። በኢትዮጵያ ምድር እናቱን ኢትዮጵያን የማይመስል ትውልድ ሻሸመኔ ላይ አደባባይ ላይ በጉልህ ታየ። እኔ በግሌ ገና ሲጸነስ ይህ ሊመጣ እንደሚችል ፍርሃት አድሮብኝ ስለነበር ብዙም አልደነቀኝም። ብዙ ሰው ከሚሰማው ይልቅ የሚያየው ያሳምነዋል። በዚህ ምክንያት በሻሸመኔ አንድ ወጣት የቁልቁሊት ተሰቅሎ ደሙ እየፈሰሰ ነገር ግን በዙሪያው የእናቱ ልጆች የደም ጥማታቸው ገና ባለመርካቱ ከመስቀል አውርደው አስከሬኑን በመኪና እየጎተቱ ከተማቸውን በደም ሊያጥቡ ሲዘጋጁ ይታዩ ነበር። ይህ በአቤል እንዲሁም በዮሴፍ ተደርጓል። "፤ ቃየንም ወንድሙን አቤልን። ና ወደ ሜዳ እንሂድ አለው። በሜዳም ሳሉ ቃየን በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት፥ ገደለውም። " (ዘፍ 4: 8) ። "እነርሱም በሩቅ ሳለ አዩት፥ ወደ እነርሱም ገና ሳይቀርብ ይገድሉት ዘንድ በእርሱ ላይ ተማከሩ። አንዱም ለአንዱ እንዲህ አለው። ያ ባለ ሕልም ይኸው መጣ። አሁንም ኑ፥ እንግደለውና በአንድ ጕድጓድ ውስጥ እንጣለው። ክፉ አውሬም በላው እንላለን፤ ዘፍ 37፥18
የወጣትነት እድሜ አዲስ ነገር ገንዘብ የሚያደርጉበት የእድሜ ክልል ነው። በአግባቡ ማግኘት የሚገባውን ትምህርት አግኝቶ በጎ ነገር መቅሰም ካልቻለ ያገኘውን ሁሉ ለመሰብሰብ ይገደዳል። በሀገራችን የሆነው ይህ ነው። ትምህርት ቤት ይዘጋል እንጅ የዘረኝነት ሚዲያው ክፍት ነበር። አስተማሪዎች መደበኛ ትምህርት መስጠት ያቁሙ እንጅ ጥላቻን ለመስበክ ብዙ መንገዶች ክፍት ነበሩ። ስለዚህ ዛሬ ላይ በዘር፣ በሃይማኖት፣ በጎሳ፣ በቋንቋ፣ ወ.ዘ.ተ ተለያይተን አንዱ አንዱን ቢበቀል ሊገርመን አይገባም። ትላንት ብዙ ሰዎች ሲጮኹ የነበረውእኮ ይኽ እንዳይደርስ በመፍራት ነበር። ዛሬ ሰዎች ስለመገንጠል ጥያቄ አነሱ ማለት እንዴት ይቻላል? ከበፊት እነሱ መቼ እንገንጠል ብለው ጥያቄ አቀረቡ? መገንጠል የሚባል መብት ሰጥቻችኋለሁ እያለ የሚያቅራራው ህገ መንግሥታችን መስሎኝ? ስለዚህ ኃላፊነት የሚሰማው መንግሥት ካለ ይኽን ደም የጠማው ሥርዓት አስተካክሎ ወደ ቀደመው አንድነታችን ይመልሰን ዘንድ ይገባል። ይህ ካልሆነ ህዝብ መፈናቀሉ፣ አብያተክርስቲያናት መቃጠላቸው፣ ካህናትና ምእመናን መታረዳቸው፣ አንዱ በአንዱ ላይ ጦር መምዘዙ የማይቆም እዳ ነው የሚሆነው።
በእኔ እምነት ዛሬ ለዚህ ለከፋ ችግር ውስጥ ለመግባታችን መንግስታትን ብቻ በመውቀስ ለውጥ የማያመጣ ትችት በመሰንዘር ብቻ ማቆም ያለብን አይመስለኝም። ትውልድ የሚታነጸው በሃይማኖት መምህራን፣ በዘመናዊ የትምህርት ተቋማት፣ በወላጆች እና በሀገር ወዳድ ህዝቦች መሆኑ የታወቀ ነው። ይሁን እንጅ እነዚህ አካላት በመንግሥት የተጣመመ ሥርዓት ምክንያት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ አልቻሉም። ነገር ግን ከተጣለባቸው ኃላፊነት አንጻር መስዋእትነት ከፍለው ትውልድን ማትረፍ ግዴታቸው በመሆኑ ከተጠያቂነት ሊያመልጡ አይችሉም። ይህ ድክመት ያመጣውን ውድቀት ለማየት በመቻላችን እንዳይደገም ነቅተን ትውልዱን ለማነጽ መስራት ይጠበቅብናል።
ያለንበት ወቅት መረጃ በፍጥነት የሚዳረስበት በመሆኑ እንጅ ባለፉት ዘመናትም በተለያየ ጊዜ አጥፊዎች በተደራጀ ሁኔታ የጥፋት ዓላማቸውን ሲፈጽሙ ሲያስፈጽሙ ነበር። ሰው እንደ እንስሳ፣ እንደ አውሬ ሌት ከቀን የማይጠበቅ ሆኖ ነው እንጅ የዛሬዎቹ አጥፊዎች ትላንትም ነበሩ። "ህልም አለ ተብሎ ሳይተኛ አይታደርም" እንዲሉ እነሱን በመፍራት በተወለዱበት ሀገር አለመኖር አይቻልም እንጅ ትላንትናም የሚያጠፉትን አጥፍተው ዛሬ ላይ የደገሙትን እንደሚያደርጉ ይፎክሩ ነበር። ሰው የሚኖረው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና ነገንም እንድንኖር የነሱ ፍላጎት ባይሆንም በእግዚአብሔር ቸርነት እንኖራለን።
ኢትዮጵያዊ ሆይ ሰው ሆነህ ተፈጥረሃልና ሰው ሁነህ ሙት። የተሰጠህን ማንነት ጥለህ ያልተሰጠህን አትፈልግ። ይህ ወደር የማይገኝለት ውርደት ነው። ዲያቢሎስ ያልተሰጠውን ሽቶ በድሎ ከሰማይ ወደ ምድር ወርዷልና። ኢትዮጵያዊነት ማንነትህ ነው። በየዘመኑ የተነሱ መሪዎች የሰጡህ ሳይሆን ፈጣሪ ከኢትዮጵያ ምድር እንድትበቅል ፈቃዱ ስለሆነ እንጅ የማንም ፍላጎት የለበትም። ይኽን አትዘንጋ። ኢትዮጵያዊነትን ትቶ በዘር በቋንቋ መመካት ከሰማይ ወደ ምድር የመውደቅ ያክል ውርደት ነው። "አያያዙን አይቶ ጭብጦውን ቀማው" እንዲሉ፤ በኢትዮጵያውያዊነትህ መኩራት ስታቆም ምንደኛች ማንነትህን ነጥቀው ያንተ ያልሆነ ማንነት አስጨብጠውሃል። ለአንተ አስበው ሳይሆን ስውር ዓላማቸውን መፈጸሚያ አድርገውሃል። እንደ ቦይ ውሃ የምትነዳ አትሁን። አባቶቻችን እነ አፄ ዮሐንስ አንገታቸው የተቆረጠው ኢትዮጵያዊ ተብለው ነው። ጀግናው ቴዎድሮስ ጥይቱን የጠጣው ስለ ማንነቱ ነው። ማንነቱ ደግሞ ኢትዮጵያ ነች። እምየ ምንይልክ አድዋ የዘመተው ለማንነቱ ነው። እግዚአብሔርን ይዞ ድንቅ ታሪክ አኑሮ አልፏል። ወገኔ በውሸት ታሪክ እንዳትታለል ያ ታሪክ ያንተም ታሪክ ነው። ኃይለ ሥላሴ በዓለም ስሟን ያስጠራት ኢትዮጵያ ልዩ ነች። እነዚህን መሪዎች ስናስብ አንዲት ኢትዮጵያን እናስባለን። ከእነዚህ መሪዎች ጋር የነበሩትን ኢትዮጵያውያንንም እናስባለን። ሌሎችንም ለቅድስት ሀገራቸው ኢትዮጵያ ዘመን ሊሽረው የማይችል ታሪክ የሰሩትን ሁሉ እንዳልዘረዝር ጽሁፌ አንባቢ ያጣል። ይሁን እንጅ ታሪካቸው እስከ ዓለም ፍጻሜ ሲዘከር ይኖራል። ኢኢትዮጵያዊ መባል በምድር ላይ ምን ያህል ክብር እንዳለው ለማወቅ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ይጠቅማል። ዘፍ 2፥13 / ዘኁል. 12፥1/ ኢዮብ 28፥19/ መዝ 68፥31 መዝ 72፥9 መዝ 74፥14 ኢሳ 18፥1 ኤር 13፥23 ኤር 38፥7 ኤር 39፥7 አሞ 9፥7። ሶፎ 3፥10 የሐ ሥ 8፥27።
ወገኔ ሆይ ስማኝ ላስታውስህ በሰፈርክበት መስፈሪያ ይሰፈርብሃልና አስተውል። ይህች ዓለም የኮንትራት ቤትህ ነች። ዘለዓለም ለመኖር እድል በሌላት ህይዎትህ ኃጢአትን አታብዛ። ወደድክም ጠላህም እውነታው ይኽ ነው" "፤ አፈር ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህ። "( ዘፍ 3: 19)
መ/ሃይማኖት ቀሲስ ዘለዓለም ጽጌ
St louis Missouri
U.S.A
መ/ሃይማኖት ቀሲስ ዘለዓለም ጽጌ
St louis Missouri
U.S.A
No comments:
Post a Comment