ሰውና እንስሳ ከሚለዩባቸው ነገሮች አንዱና ዋናው ነገር የሰው ልጅ የሚጠቅመውንና የማይጠቅመውን ለይቶ ማወቅ መቻሉ ሲሆን እንስሳት ግን ይህን የሚያውቁበት አእምሮ ስለሌላቸው በሰው ፈቃድና ፍላጎት ስር መሆናቸው ነው። ብዙ ጊዜ ረጋ ብሎ የሰሩት ነገር ፍሬያማ ይሆናል። የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል አደል የተባለው፥ ቀደም ሲል የነበሩት አባቶቻችን ሃገር ሲመሩ፣ ቤተክርስቲያንን ሲመሩ፣ ቤተሰብን ሲመሩ ቆም ብሎ የማሰብ ትልቅ ጸጋ ነበራቸው። ለዚያ ነው ዛሬም ድረስ ያ አሻራ ለትውልድ ተላልፎ ወደ ስህተት የሚጓዝን ሰው ቆም ብለህ አስብ ፣ ቆም ብለሽ አስቢ፣ ቆም ብላችሁ አስቡ እየተባለ በምሳሌ የሚነገረው።
Friday, March 30, 2012
Sunday, March 18, 2012
የዕለቱ ወንጌል
ማቴ 24፥1
1 ኢየሱስም ከመቅደስ ወጥቶ ሄደ፥ ደቀ መዛሙርቱም የመቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት ቀረቡ።
2 እርሱ ግን መልሶ። ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አላቸው።
3 እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው። ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።
4 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው። ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።
1 ኢየሱስም ከመቅደስ ወጥቶ ሄደ፥ ደቀ መዛሙርቱም የመቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት ቀረቡ።
2 እርሱ ግን መልሶ። ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አላቸው።
3 እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው። ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።
4 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው። ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።
Saturday, March 17, 2012
የእንጀራ ልጆች
በየትኛውም ማህበረሰብ ውስጥ ድርጊትን የሚያመለክቱ የተለያዩ የመገለጫ ቋንቋዎችን ወይንም ደግሞ ስሞችን እናገኛለን በእኛ ሀገርም ድርጊታዊ ሁኔታዎችን መሰረት ያደረጉ የተለያዩ ስሞችን እንጠቀማለን ከነዚህም አንዱ << የእንጀራ ልጅ >> የሚለው ነው።
የእንጀራ ልጅ ከስሙም እንደምንረዳው እውነተኛ ልጅ ያልሆነ እና እናት የተባለችውም የልጆች አባት የሆነ ባል ስላገባች እንዲሁም እንደወለደቻቸው ልጆቿ አድርጋ እንጀራ ስላበላች እንጅ ስለወለደች አይደለም ። የእንጀራ ልጅ ሁልጊዜ ለእንጀራ እናቱ የሚሰጣት ፍቅር በምታበላው እንጀራ ይወሰናል። እስኪጠግብ የበላ እለት እናቴ ይላታል አንድ ቀን የጎደለበት ጊዜ ግን ስሟን ማጥፋት ይጀምራል። ምክንያቱም ያገናኛቸው እንጀራ እንጅ በስጋ 9 ወር ከ 5 ቀን በማህጸኗ ተሸክማ አልወለደችውም። ከስጋዋ ስጋን ከነፍሷ ነፍስን የወሰደ ቢሆን ግን አካሉ ነችና ህመሟ ያመዋል፣ ደስታዋ ያስደስተዋል፣ ስሟ በክፉ ሲነሳ አይወድም፣ ከራሱ በላይ አብልጦ ይወዳታል። የእንጀራ ልጅ ግን ከሷ የተሻለ የምታበላው የምትንከባከበው ካገኘ ያችንም እናቴ ነሽ ይላታል። ነገር ግን አሁንም ጥቅሙ ከቀረበት ሌላ ፍለጋ መሄዱ አይቀርም ምክንያቱም መሰረታዊ ግንኙነታቸው ጥቅም ስለሆነ ማለት ነው። አንድ ኢትዮጵያዊ ምሁር በአንድ ወቅት የተናገሩትን አስታውሳለሁ << አንድ ሰው ለጥቅም ብሎ እግዚአብሔርን የሚያገለግል ከሆነ የተሻለ ጥቅም ካገኘ ሰይጣንንም ከማገልገል ወደኋላ አይልም ብለው ነበር >> ስጋዊ ጥቅም ከእግዚአብሔር መንግስት ይለያል። ሰው ደግሞ ከእግዚአብሔር መንግስት ከተለየ ሰው መባሉ ከንቱ ነው። በተለይ እንኳን የእግዚአብሔርን ቤት ለማገልገል የተመረጠ ይቅርና በክርስቶስ ክርስቲያን ተብሎ በስሙ የከበረ ሁሉ በስጋዊ ጥቅም መታለል አይገባውም። ይህን ስል በህይዎታችን የምናውቃቸው ብዙ መልካም ሰዎች ይኖራሉ ። የእናትን ውለታ ስለተረዱ ሴት ለተባለች ሁሉ ክብር የሚሰጡ፣ የእንጀራ እናታቸውን ከወለደቻቸው ልጆቿ አብልጠው የሚንከባከቡ እንዳሉ ባለመዘንጋት ነው። Wednesday, March 7, 2012
ስምና ተግባር
ስም( noun) መጠሪያ መለያ መገለጫ ወ , ዘ , ተ , ልንለው እንችላለን። በቀደመው ዘመን ስም ይሰጥ የነበረው ከተግባር ጋር ተያይዞ እንደነበር ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል ። በተለያየ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ከመልካም ስራቸው የተነሳ እግዚአብሔር አዲስ ስም የሰጣቸው ሰዎች እንዳሉም እናያለን። አብርሃምና ሳራ << ከዛሬም ጀምሮ እንግዲህ ስምህ አብራም ተብሎ አይጠራ፥ ነገር ግን ስምህ አብርሃም ይሆናል ለብዙ አሕዛብ አባት አድርጌሃለሁና። ዘፍ 17፥5 እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፦ የሚስትህን የሦራን ስም ሦራ ብለህ አትጥራ፥ ስምዋ ሣራ ይሆናል እንጂ። ዘፍ 17፥15 ፣ ያዕቆብ << እግዚአብሔርም፦ ስምህ ያዕቆብ ነው ከእንግዲህም ወዲህ ስምህ ያዕቆብ ተብሎ አይጠራ፥ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ አለ ስሙንም እስራኤል ብሎ ጠራው። ዘፍ 35፥10 >> ቅ/ጳውሎስ የሐዋ ሥ 13፥9፣ ቅ/ጴጥሮስ ማቴ 16፥6
ከእግዚአብሔር ቀጥሎ አዳም ለፍጥረታት ሁሉ መጠሪያ እንደሰጣቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፏል። ይህም ገዥነቱን አስተዳዳሪነቱን ያመለክታል። << እግዚአብሔር አምላክም የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ሁሉከመሬት አደረገ በምንስም እንደሚጠራቸውም ያይ ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው አዳምም ሕያው ነፍስ ላለው ሁሉ በስሙ እንደጠራው ስሙ ያው ሆነ። አዳምም ለእንስሳት ሁሉ፥ ለሰማይ ወፎችም ሁሉ፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ ስም አወጣላቸው ዘፍ 2፥19 >>
Subscribe to:
Posts (Atom)