Saturday, July 2, 2011

የባርነታችሁን ቀንበር ሰብሬያለሁ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

 ባሪያዎች እዳትሆኑአቸው ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ የባርነታችሁን ቀንበር ሰብሬአለሁ ቀና ብላችሁ እንድትሄዱ አድርጌአችኋለሁ። ዘሌ 26፥13

ይህንን ቃል የተናገረው እግዚአብሔር አምላካችን በባሪያው በሊቀ ነቢያት ሙሴ አማካኝነት ነው እስራኤላውያን በግብጽ ባርነት ለ400 ዓመት ከቆዩ በኋላ መከራው ስለጸናባቸው ወደ እግዚአብሔር ጮሁ እግዚአብሔርም ጩኸታቸውን ሰምቶ በሊቀ ነቢያት ሙሴ አማካኝነት ታላላቅ ተአምራትን አድርጎ ከግብጽ ምድር አወጣቸው በግብጽ በረሃ ከዓለት ላይ ውሃ እያፈለቀ ከደመና መና እያወረደ እየመገበ ወደ ተስፋይቱ ምድር  ጉዞ ጀምረው ነበረ ይሁን እንጅ ህዝበ እስራኤል እግዚአብሔር ያደረገላቸውን ውለታ በመዘንጋት ወደ ጣኦት አምልኮ ፊታቸውን በማዞራቸው እግዚአብሔር ተቆጥቷቸዋል

Friday, July 1, 2011

የዘላለም ሕይዎት

የዘላለም ህይዎትን እንድዎርስ ምን ላድርግ ?

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳም የገባውን ቃል ሊፈጽም ሰው በሆነበት ዘመን  በሰፊው ያስተምር የነበረው የዘለዓለም ህይወትን ሊሰጥ እንደመጣ ነበር። ነገር ግን ብዙዎች የቃሉን ትምህርት የእጁን ተአምራት እያዩ ቢያምኑበትም እስከ መጨረሻው የተከተሉት ጥቂቶች ነበሩ። ስለ ዘላለም ህይወት አራቱም ወንጌላውያን በሰፊው ጽፈዋል። ወንጌላዊው ሉቃስ የጻፈውን እናስቀድም ,, ከአለቆችም አንዱ። ቸር መምህር፥ የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ? ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስም፦ ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም። ትእዛዛቱን ታውቃለህ፥ አታመንዝር፥ አትግደል፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥ አባትህንና እናትህን አክብር አለው። እርሱም፦ ይህን ሁሉ ከሕፃንናቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ አለ። ኢየሱስም ይህን ሰምቶ። አንዲት ገና ቀርታሃለች፤ ያለህን ሁሉ ሽጠህ ለድሆች ስጥ፥ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ አለው። እርሱ ግን ይህን ሰምቶ እጅግ ባለ ጠጋ ነበርና ብዙ አዘነ። ኢየሱስም ብዙ እንዳዘነ አይቶ። ገንዘብ ላላቸው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ይሆናል። ባለ ጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ሊገባ ይቀላል አለ። ሉቃ 18፥18