ይህ ወቅት በቤተክርስቲያናችን በዓለም ውስጥ ላሉ ሁሉ ፍጥረታት ሰላምና ፍቅርን በረከትን እንዲያገኙ ወደ ፈጣሪያችን
በጾም በጸሎት ተወስነን ልመና የምናቀርብበት ጊዜ ነው። ታዲያ በዚህ ጊዜ የሰው ልጅ ሁሉ ጠላት የሆነው ሰይጣን ዲያብሎስ በተለያየ መንገድ
ከዓላማችን ወደ ኋላ እንድንል የማይቀይሰው መንገድ አይኖርም። ስለዚህ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ “መጋደላችን ከደምና
ከሥጋ ጋር
አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት
ጋር ከዚህም
ከጨለማ ዓለም ገዦች
ጋር በሰማያዊም
ስፍራ ካለ
ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት
ጋር ነው
እንጂ ኤፌ 6፥12 ” እንዳለው በክርስትና ህይዎት ስንኖር ብዙ ልዩ ልዩ ዓይነት ፈተና
ሊገጥመን ይችላል። ይህን ፈተና የምናልፍበት ጥበብና ማስተዋል ከሌለን ጠልፎ ሊያስቀረን ይችላል።